Good News·3 ከ 4

God's Rescue Plan

Have you ever felt like the world was broken, and that we are broken along with it? Often, our attempts to fix the world and ourselves only lead to more problems. But there is Good News: God, in His love, has made a way for us to be restored to honor.

የእርስዎን ይጠይቁ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

አጋራ
Romans 6:23

For the wages of sin is death, but the gift of God is eternal life in Christ Jesus our Lord.

Berean Standard Bible

Public Domain

ተጨማሪ አንብብ...
1 John 5:11

And this is that testimony: God has given us eternal life, and this life is in His Son.

Berean Standard Bible

Public Domain

ተጨማሪ አንብብ...
1 John 5:13

I have written these things to you who believe in the name of the Son of God, so that you may know that you have eternal life.

Berean Standard Bible

Public Domain

ተጨማሪ አንብብ...
ነፃ ምንጮች

መጽሐፍ ቅዱስን ይበልጥ በጥልቀት ማስተዋል ይፈልጋሉ?

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችንን ይቀላቀሉ

ጽሑፍ ቅጂ

Amharic (ኣማርኛ)
አንዳንድ ጊዜ አለማችን ከጥቅም ውጪ የሆነች ያህል አይሰማህም? ልክ ያልሆነ ነገር እንዳለ አይነት በመጀመሪያ እግዚአብሔር ምድርን በመልካም ነገር የተሞላችእንድትሆን አድርጎ ፈጠራት ነገር ግን እኛ ከርሱ ይልቅ የራሳችንን መንገድ በመከተል እግዚአብሔርን አልታዘዝንም አለማችን ከጥቅም ውጪ ሆነች፤ እኛም እንደዚያው መፅሐፍ ቅዱስ ይህንን ሃጥያት ብሎ ይጠራዋል ከድርጊታችን አልፎም የልባችን አመለካከት ሆነ ለአለመታዘዛችን ተፈጥሮአዊው ውጤት ሞት ነው፡፡ ከህይወት ምንጭ ጋር መለያየት ያንንም መለያየት እንደ የጥፋተኝነት፥ ሃፍረትና ያለመንፃት ስሜቶች ሲሰሙን ማስተዋል እንችላለን ነገር ግን ሃጥያታችንን ለማስወገድና ለመታደስ ማድረግ የምንችለው ምንም ነገር የለም ከቅዱሱ እግዚአብሔር ጋር እስከተለያየን ድረስ ታሪካችን እዛ ጋር ካበቃ አሳዛኝ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር መንገድ አዘጋጅቷል፡፡ ገና ከመጀመሪያው እግዚአብሔር የማዳን ዕቅድ ነበረው እግዚአብሔር ለአባቶቻችን ይህንን ዕቅዱን ገለጠላቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ፥ አብርሃም በእግዚአብሔር ፊት በእምነት ፃድቅ ሰው ነበረ እግዚአብሔርን በመታዘዝ፥ ልጁን መስዋዕት ለማድረግ አብርሃም ፈቃደኝነት ማሳየቱን እግዚአብሔር አከበረለት ነገር ግን በእግዚአብሔር ጣልቃገብነት፥ በልጁ ፈንታ እንዲሰዋ በግን አቀረበ እግዚአብሔር ፃድቅ ነው፤ ስለዚህም እኛ ሞትና ከእግዚአብሔር ጋር ልንለያይ ይገባናል ነገር ግን እግዚአብሔር ይወደናል፤ እኛም ከእርሱ ጋር የዘላለም ህይወት እንዲኖረን ይፈልጋል፡፡ ልክ እግዚአብሔር የአብርሃምን ልጅ መስዋዕትነት በተዓምራዊው በግ እንደተካው እግዚአብሔር ኢየሱስን የመጨረሻው ፍፁም መስዋዕት አድርጎ አቅርቦልናል ኢየሱስ ሃጥያታችንን ሸፈነ፤ የሃጥያት ደመወዝ ከሆነው ሞት ነፃ አወጣን እናም ፃድቃን አደረገን፡፡ ፍፁም አምላክ የሆነው ኢየሱስ፤ ወደዚህችየፈራረሰች አለም ፍፁም ህይወት ለመኖር ፍፁም ሰው ሆኖ መጣ በሞቱ የኛን ነቀፋ እና ቅጣት ወሰደ ለኛ የሚገባንን ሞት እርሱ ሞተ ድጋሚ ላይሞት ከሶስት ቀን በኋላ ከሞት ተነሳ ይህ የመፅሐፍ ቅዱስ የምስራች ነው ከርሱ ጋር የዘላለም ህይወት እንዲኖረን እግዚአብሄር መንገድ አዘጋጅቶልናል እምነታችሁን እግዚአብሄር በክርስቶስ በኩል ባደረገላችሁ ላይ ስታደርጉ ነቀፋችሁን በክብር፤ ጥፋተኝነታችሁን በፅድቅ ይለውጠዋል መፅሐፍ ቅዱስ «የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የፀጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው፡፡» ይላል ነገር ግን ይህ ስጦታ የናንተ የሚሆነው ስትቀበሉት ብቻ ነው ይህንንም በማንኛውም ሰዓት በመፀለይ መቀበል ትችላላችሁ
JesusFilm