Relationships·7 ከ 9

Birth of Jesus

Luke makes his introduction as the careful author of this Gospel. The angel Gabriel appears to Mary, a virgin in Nazareth. He announces to her that she has found favor with God and will give birth to Jesus, the Son of God. Through Jesus' birth, prophecies are fulfilled by the arrangement of events. God leaves no detail unnoticed. The same can be said of our own lives.

የእርስዎን ይጠይቁ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

አጋራ
Luke 1:1

Many have undertaken to compose an account of the things that have been fulfilled among us,

Berean Standard Bible

Public Domain

ተጨማሪ አንብብ...
ነፃ ምንጮች

መጽሐፍ ቅዱስን ይበልጥ በጥልቀት ማስተዋል ይፈልጋሉ?

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችንን ይቀላቀሉ

ጽሑፍ ቅጂ

Amharic (ኣማርኛ)
የተወደድክ ቴዎፍሎስ ሆይ! በመካከላችን ስለተፈፀመው ሁሉ ፍፁም እውነቱን እንድታውቅ ነገሮችን በቅደም ተከተል አድርጌ በየተራው እፅፍልሃለሁ፡፡ አውግስጦስ ቄሳር የሮም ንጉስ በነበረበት ዘመን፣ ታላቁ ሄሮድስም ይሁዳን ይገዛ በነበረበት ዘመን መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ከተማ ስሟ ማሪያም ወደምትባል አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፡፡ ማሪያም ሆይ አትፍሪ! በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ አግኝተሻልና! እነሆ ትፀንሻለሽ፣ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፣ ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ፡፡ ይህ እንዴት ይሆናል? እኔ ድንግል ነኝ:: መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል። በዚህም ምክንያት ቅዱሱ ህፃን የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ይባላል። ለመንግስቱም ፍፃሜ የለውም። ማርያምም የመውለጃ እድሜዋ ያለፈባትን ነገር ግን በእግዚአብሔር ተዓምር የፀነሰችውን ዘመዷን ኤልሳቤጥን ለመጎንኘት ሄደች። ኤልሳቤጥ! ማርያም! እህቴ ማሪያም! አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተባረክሽ ነሽ፡፡ የምትወልጂውም ልጅ የተባረከ ነው። ልክ ሰላምታሽን እንደሰማሁ፤ በማህፀኔ ያለው ፅንስ በደስታ ዘለለ፡፡ ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፡፡ መንፈሴም በአምላኬና በመድሀኒቴ ሀሴት ታደርጋለች፡፡ ከአሁን ጀምሮ የሚመጣው ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ናት ይሉኛል፡፡ አዋጅ፣ አዋጅ ለናዝሬትከተማ ነዋሪዎች በሙሉ! ህዝብ ሁሉ ይቆጠር ዘንድ ከአውግስጦስ ቄሳር ትዕዛዝ ስለወጣ በይሁድና በገሊላ የምትኖሩ ህዝቦች ሁሉ በየአባቶቻችሁ የትውልድ ሀገር እየሄዳችሁ እንድትመዘገቡ ተብሎአል፡፡ ዮሴፍም ከእጮኛው ከማሪያም ጋር ሊመዘገብ ወደ ይሁዳ ከተማ ወደ ቤተልሄም ሄደ፡፡ በቤተልሄምም ስፍራው ሁሉ ሞልቶ ነበርና ማደሪያ አላገኙም። ያገኙት ማረፊያ የከብቶች በረት ብቻ ነበረ፡፡ በዚያም መንደር ለሊቱን በሙሉ መንጋዎቻቸውን በትጋት የሚጠብቁ እረኞች ነበሩ፡፡ በድንገትም፤ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠላቸው፤ የእግዚአብሔርም ክብር በዙሪያቸው አበራ፡፡ ዛሬ በዳዊት ከተማ አዳኛችሁ ተወልዶአል። እርሱ ጌታ የሆነው ክርስቶስ ነው። እረኞቹም በግርግም የተኛውን ህፃን ለማየት ፈጥነው ሄዱ፤ ስለአዳኙም መወለድ የምስራቹን ዜና ለማብሰር የመጀመሪያዎቹ ሆኑ።
JesusFilm