JESUS·61 ምዕራፎች

This film is a perfect introduction to Jesus through the Gospel of Luke. Jesus constantly surprises and confounds people, from His miraculous birth to His rise from the grave. Follow His life through excerpts from the Book of Luke, all the miracles, the teachings, and the passion. God creates everything and loves mankind. But mankind disobeys God. God and mankind are separated, but God loves mankind so much, He arranges redemption for mankind. He sends his Son Jesus to be a perfect sacrifice to make amends for us. Before Jesus arrives, God prepares mankind. Prophets speak of the birth, the life, and the death of Jesus. Jesus attracts attention. He teaches in parables no one really understands, gives sight to the blind, and helps those who no one sees as worth helping. He scares the Jewish leaders, they see him as a threat. So they arrange, through Judas the traitor and their Roman oppressors, for the crucifixion of Jesus. They think the matter is settled. But the women who serve Jesus discover an empty tomb. The disciples panic. When Jesus appears, they doubt He's real. But it's what He proclaimed all along: He is their perfect sacrifice, their Savior, victor over death. He ascends to heaven, telling His followers to tell others about Him and His teachings.

የእርስዎን ይጠይቁ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

አጋራ
ነፃ ምንጮች

መጽሐፍ ቅዱስን ይበልጥ በጥልቀት ማስተዋል ይፈልጋሉ?

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችንን ይቀላቀሉ

ጽሑፍ ቅጂ

Amharic (ኣማርኛ)
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ዓለምን ፈጠረ፤ እርሱም ሰማያትንና ምድርን በውስጣቸው ያለውን ሁሉ ፈጠረ፡፡ እግዚአብሔር የሠራውን ሥራ ሁሉ ስንመለከት እጅግ እንደነቃለን፡፡ እግዚአብሔር የሠራው ሁሉ መልካም ነበር፡፡ ሁሉ የእርሱን ታላቅነት፣ መልካምነትና ኃይል ይገልጣሉ፡፡ እግዚአብሔር የተለያዩ ዝርያ ያላቸውን የዕጽዋትንና እንስሰሳት ሁሉ ፈጠረ ከዚያም የመጀመሪያውን ሰው ከምድር አፈር አበጀው፡፡ በአፍንጫውም የሕይወትን እስትንፋስ እፍ አለበት ሕይወትንም ሰጠው ይህም የመጀመሪያው ሰው አዳም ይባላል ከዚያ እግዚአብሔር ሴትን የአዳም ሚስትና ረዳት እንድትሆን ፈጠራት፡፡ ሔዋን ተብላም ተጠራች፡፡ እግዚአብሔርም ወንድና ሴት አድርጎ በአምሳሉ ፈጠራቸው ስለዚህም ከእርሱ ጋር የቅርብ ግንኙነት ነበራቸው፡፡ ውብ በሆነችው ገነት ውስጥ ከእርሱ ጋር በደስታ ይኖሩ ነበር፡፡ በዚያም መከራና ሞት አልነበረም፡፡ እግዚአብሔር አዳምን "ከአንዷ በስተቀር ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፡፡ ከእርሷ በበላህ ቀን ግን ትሞታለህ" አለው፡፡ ነገር ግን አንድ ቀን ሰይጣን የአጋንንቶች አለቃ ሔዋንን ፈተናት፡፡ እርሷም ከፍሬው ጥቂት ወስዳ በላች ባሏም ደግሞ በላ፡፡ በዚያች ቅጽበት ከእግዚአብሔር ጋር የነበራቸው ግንኙነት ተቋረጠ እግዚአብሔር ቅዱስ ነው፣ ኃጢአተኞች ከእርሱ ጋር መኖር አይችሉም፡፡ እግዚአብሔርም አዳምንና ሔዋንን ገነት አባረራቸው፡፡ እግዚአብሔርን ባለመታዘዛቸው ይህ ሁሉ ኃፍረት መጣባቸው፡፡ በውጤቱም አዳምና ሔዋን፣ ዘራቸውም በጠቅላላ በህመምና በሞት ይሰቃይ ጀመር፡፡ እግዚአብሔር ግን ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር አልቀነሰም፡፡ ስለዚህም ተመልሰው ከእርሱ ጋር መኖር የሚችሉበትን መንገድ አዘጋጀ፡፡ እግዚአብሔር የሰውን ዘር ከኃጢአት ለማዳን ያዘጋጀውን እቅድ በቅዱሳት መጻፍት በኩል አስታውቋል። እግዚአብሔርም ከዕቅዱ መካከል አንዱን ክፍል ለነቢዩ አብርሃም አሳወቀ። አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ አከበረውም፡፡ እግዚአብሔርም እንደሚባርከውና የምድርንም ህዝቦች ሁሉ በእርሱ በኩል እንደሚባርክ ቃል ገባለት፡፡ በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ በሰማይ እንዳሉ ከዋክብት ... ዘሩንም እንደሚያበዛለት ቃል ገባለት። አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ፡፡ ከእምነቱም የተነሳ እግዚአብሔር ጻድቅ ነህ ብሎ አወጀለት፣ ሰዎችም "የእግዚአብሔር ወዳጅ" ብለው ጠሩት አንድ ቀን እግዚአብሔር በእርሱ መታመኑንና ትዕዛዛቱንም እንደሚጠብቅ ለማወቅ አብርሃምን ፈተነው፡፡ ልጁንም ወስዶ እንዲሰዋለት አዘዘው፡፡ አብርሃምም በዚሁ አንድ ልጁ በኩል ዘሩ እንደሚበዛ እግዚአብሔር ቃል እንደገባለት እያወቀ እግዚአብሔርን በማመን ታዘዘ፡፡ ስለዚህም ልጁን ለእግዚአብሔር መስዋዕት አድርጎ ለመግደል ተዘጋጀ፡፡ እግዚአብሔር ግን "አብርሃም! በልጁ ላይ አንዳች አታድርግበት፡፡]Nእኔን እንደምትፈራና ልትታዘዘኝም ዝግጁ እንደሆንክ አወቅሁ" አለው አብርሃምም አንድ አውራ በግ አየ፡፡ ቀንዶቹም በቁጥቋጦ ተጠላልፈው ነበር፡፡ አብርሃምም እግዚአብሔር ያዘጋጀውን አውራ በግ ወስዶ በልጁ ምትክ ለእግዚአብሔር መስዋዕት አደረገው፡፡ እግዚአብሔር በጉን በአብርሃም ልጅ ምትክ መስዋዕት ሆኖ እንዲሞት በማቅረብ፤ ለሰዎች ያለውን ታላቅ ፍቅር አሳየ፡፡ የእርሱም ፍቅር መልካም አባት ለልጆቹ ያለውን አይነት ነው በዚህም እግዚአብሔር በሰው ልጆች ምትክ የፍፃሜ መስዋዕት ለማቅረብ ያዘጋጀውን ዕቅድ ገለጠ፡፡ ከብዙ ዘመናት በፊት እግዚአብሔር የአዳምን ዘር ኃጢአትና ኃፍረት እንዲያስወግድ፤ በእነርሱም ምትክ መስዋዕት እንዲሆን አንዳች ኃጢአት የሌለበትን ሰው እንደሚልክ ለነቢያት ገለጠላቸው፡፡ የእርሱም፣ ስዋዕትነት በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር በህብረት ለዘላለም መኖር የሚችሉበትን መንገድ ይከፍታል፡፡ ነቢያትም ይህንን ሰው "መሲሁ" ብለው ይጠሩታል፡፡ እግዚአብሔር ሰዎችን እንዲያድንና በእግዚአብሔር ስም ለዘለዓለም እንዲገዛቸው መሲሁን ይልካል ብለው ተናገሩ፡፡ ከመምጣቱ ከብዙ መቶ አመታት ቀደም ብሎ፣ ነቢያቱ መሲሁ ስለሚያከናውናቸው ተግባራትና በእርሱም ላይ ስለሚደርስበት ነገሮች ተናገሩ፡፡ ከነቢያት አንዱም እግዚአብሔር መሲሁን "አንተ ልጄ ነህ" ብሎ አወጀ ሲል ይናገራል፡፡ "የእግዚአብሔር ልጅ" የሚለው መጠሪያ መሲሁ ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን የቅርብ ግንኙነትና እንደ አዳኝና ንጉስ ያለውን ድርሻ የሚያመለክት ነው፡፡ ኢሳያስ የተባለው ነቢይ ደግሞ "ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች" ሲል ተናረገ፡፡ ይህም ልጅ የእግዚአብሔር ዘላላማዊ ቃል ሲሆን እግዚአብሔርም ሰው ሆኖ እንዲወለድና እግዚአብሔርን ለዓለም እንዲገልጥ ወደ ድንግል የላከው ነው፡፡ በተጨማሪም ነቢያቱ መሲሁ በቤተልሔም እንደሚወለድ ተናግረዋል፡፡ ወደ ኢየሩሳሌም እንደ ንጉሥ እንደሚገባ እና… ከወዳጆቹ በአንዱ እንደሚከዳና በ30 ብር እንደሚሸጥ አስቀድመው ተንብየዋል፡፡ ነቢያቱ መሲሁ ሕይወቱን መስዋዕት እንደሚያደርግ እግዚአብሔር ግን በሦስተኛው ቀን ከሙታን እንደሚያስነሳው ተናግረዋል፡፡ ነቢያቱም መሲሁን "የሰው ልጅ" ብለው ይጠሩታል ደግሞም ደመናትን ሰንጥቆ እግዚአብሔር ወዳለበት እንደሚመለስ እና እግዚአብሔር በህዝቦች ሁሉ ላይ የዘላለም ሥልጣን እንደሚሰጠው ተናግረዋል፡፡ ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት በዚህ ምድር የኖረ ስሙ ኢየሱስ የተባለ አንድ ሰው ነበረ፡፡ ሰዎችም እርሱ የሚያደርጋቸውን ነገሮች ባዩ ጊዜ እርስ በርሳቸው "ይህ ሰው መሲሁ ይሆንን?" "የኢየሱስ ሕይወት ነያብቱ ስለ መሲሁ የተናገሩት ፍፃሜ ይሆንን?" ይባባሉ ነበር፡፡ ይህ ፊልም ኢየሱስ ማን እንደሆነ እርሱ ከተናገራቸውና ካከናወናቸው ጥቂቶቹንና በቅዱሳት መጻህፍት የተጻፉትን ያቀርብላችኋል፡፡ በዚህ ፊልም እንደ ኢየሱስ ሆኖ የተወነው ሰው ነው፡፡ ይህንን ለማድረግ የተገባው ማንም የለም፣ ሆኖም ግን ይህ ፊልም ሰዎች ስለ ኢየሱስ ሕይወት እንዲያውቁና እንዲማሩ ለማድረግ የተዘጋጀ ነው፡፡ በዚሁም እግዚአብሔር ሊሰጥ ተስፋ የገባውን በረከት ይቀበላሉ፡፡ የተወደድክ ቴዎፍሎስ ሆይ! በመካከላችን ስለተፈፀመው ሁሉ ፍፁም እውነቱን እንድታውቅ ነገሮችን በቅደም ተከተል አድርጌ በየተራው እፅፍልሃለሁ፡፡ አውግስጦስ ቄሳር የሮም ንጉስ በነበረበት ዘመን፣ ታላቁ ሄሮድስም ይሁዳን ይገዛ በነበረበት ዘመን መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ከተማ ስሟ ማሪያም ወደምትባል አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፡፡ ማሪያም ሆይ አትፍሪ! በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ አግኝተሻልና! እነሆ ትፀንሻለሽ፣ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፣ ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ፡፡ ይህ እንዴት ይሆናል? እኔ ድንግል ነኝ:: መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል። በዚህም ምክንያት ቅዱሱ ህፃን የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ይባላል። ለመንግስቱም ፍፃሜ የለውም። ማርያምም የመውለጃ እድሜዋ ያለፈባትን ነገር ግን በእግዚአብሔር ተዓምር የፀነሰችውን ዘመዷን ኤልሳቤጥን ለመጎንኘት ሄደች። ኤልሳቤጥ! ማርያም! እህቴ ማሪያም! አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተባረክሽ ነሽ፡፡ የምትወልጂውም ልጅ የተባረከ ነው። ልክ ሰላምታሽን እንደሰማሁ፤ በማህፀኔ ያለው ፅንስ በደስታ ዘለለ፡፡ ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፡፡ መንፈሴም በአምላኬና በመድሀኒቴ ሀሴት ታደርጋለች፡፡ ከአሁን ጀምሮ የሚመጣው ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ናት ይሉኛል፡፡ አዋጅ፣ አዋጅ ለናዝሬትከተማ ነዋሪዎች በሙሉ! ህዝብ ሁሉ ይቆጠር ዘንድ ከአውግስጦስ ቄሳር ትዕዛዝ ስለወጣ በይሁድና በገሊላ የምትኖሩ ህዝቦች ሁሉ በየአባቶቻችሁ የትውልድ ሀገር እየሄዳችሁ እንድትመዘገቡ ተብሎአል፡፡ ዮሴፍም ከእጮኛው ከማሪያም ጋር ሊመዘገብ ወደ ይሁዳ ከተማ ወደ ቤተልሄም ሄደ፡፡ በቤተልሄምም ስፍራው ሁሉ ሞልቶ ነበርና ማደሪያ አላገኙም። ያገኙት ማረፊያ የከብቶች በረት ብቻ ነበረ፡፡ በዚያም መንደር ለሊቱን በሙሉ መንጋዎቻቸውን በትጋት የሚጠብቁ እረኞች ነበሩ፡፡ በድንገትም፤ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠላቸው፤ የእግዚአብሔርም ክብር በዙሪያቸው አበራ፡፡ ዛሬ በዳዊት ከተማ አዳኛችሁ ተወልዶአል። እርሱ ጌታ የሆነው ክርስቶስ ነው። እረኞቹም በግርግም የተኛውን ህፃን ለማየት ፈጥነው ሄዱ፤ ስለአዳኙም መወለድ የምስራቹን ዜና ለማብሰር የመጀመሪያዎቹ ሆኑ። ከሳምንትም በኋላ፣ ህፃኑ ስሙ ኢየሱስ ተባለ፡፡ ዮሴፍና ማሪያምም ህፃኑን ለእግዚአብሔር ለመስጠት ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት፡፡ በኢየሩሳሌምም ክርስቶስን ሳያይ እንደማይሞት መንፈስ ቅዱስ ተስፋ የተሰጠው ስምኦን የሚባል አንድ ሰው ነበር፡፡ አቤቱ ጌታ ሆይ! ዛሬ ባሪያህን እንደቃልህ በሰላም አሰናብተው፡፡ አይኖቼ በእርግጥ ማዳንህን አይተዋል፡፡ ይህም ልጅ በእግዚአብሔር የተመረጠ ነው፡፡ እግዚአብሔር ይባርካችሁ፡፡ በሙሴ ህግ እንደተፃፈ ስርዓቱን ሁሉ ከፈፀመ በላኃ ከኢየሩሳሌም ወደ ሀገራቸው ወደ ናዝሬት ተመለሱ፡፡ ኢየሱስም አስራ ሁለት አመት ሲሞላው ዮሴፍና ማሪያም የፋሲካን በዓል ለማክበር ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት፡፡ ሲመለሱም እሱ ከነርሱ ጋር ያለ መስሎአቸው ነበር፤ ኢየሱስ ግን በዚያው ቀርቶ ነበር፡፡ እርሱን ለመፈለግ ወደ ከተማው ተመለሱ፤ ከሦስት ቀን በኋላም በቤተ መቅደስ በአይሁድ የሃይማኖት መምህራን ጋር ተቀምጦ አገኙት፡፡ እንዲህ ያለ ጥያቄ የሚጠይቀን ይህ የማን ልጅ ነው? ልጃችን ነው። አብሮን ያለ መስሎን ነበር፡፡ አሁን አብሮን ይሄዳል። የሰሙት ሁሉ እጅግ ተደነቁ፡፡ ልጄ ሆይ! ለምን እንዲህ ታደርገናለህ? አባትህና እኔ ተጨንቀን ስንፈልግህ ነበር፡፡ ስለምን እኔን ትፈልጉኛላችሁ? እኔ በአባቴ ቤት እኖር ዘንድ እንደሚገባኝ አውቁም? ከእነርሱም ጋር ወደ ናዝሬት ተመለሰ፡፡ ኢየሱስ በጥበብና በሞገስ፣ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያድግ ነበር፡፡ ይህ የኢየሱስ እውነተኛ የህይወት ታሪክ ነው። ታሪኩም በሉቃስ ወንጌል ላይ የተመሰረተ ነው። በኢንስፓይሬሽናል ፊልምስ የቀረበ ኢየሱስ በንጉስ ጢባሪዮስ በ15ኛው የግዛት ዘመን ጴንጤናዊው ጲላጦስ የይሁዳ ገዢ በነበረ ጊዜ ሄሮድስም የገሊላ ገዢ በነበረ ጊዜ ሀናና ቀያፋም ሊቀካህናት በነበሩ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል በምድረ በዳ ወደ ዮሐንስ መጣ፡፡ እርሱ በዮርዳኖስ ወንዝ ዙሪያ ባሉት ከተሞች ሁሉ እየዞረ ከሀጢያት ስርየትና የንስሐ ጥምቀት ይሰብክ ነበር፡፡ ከሀጢያታችሁ ተመለሱ ተጠመቁ፡፡ እግዚአብሄርም በምህረቱ ይቅር ይላችኋልና፡፡ በነብዩ ኢሳይስ የትንቢት መጽሐፍ እንደተጻፈው፦ "በምድረበዳ የሚጮህ ሰው ድምጽ፡ የጌታን መንገድ አዘጋጁ ይጓዝበት ዘንድ ጥርጊያውንም አቅኑ ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይበል ኮረብታውና ተራራውም ሁሉ ዝቅ ይበል ጠማማው መንገድ ይቅና ሻካራውም መንገድ ይስተካከል የሰውም ልጆች ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ያያሉ!" ምን ማድረግ አለብን? አዎ! ምን ማደግ እንዳለብን? እናንተ የእፉኝት ልጆች! ምን እናደርግ ዘንድ ትውዳለህ? እርዳን። ከየትኛው መንገድ እንመለስ። ማንም ሁለት ልብስ ያለው አንዱን ምንም ለሌለው ሰው ሳይሰስት በልግስና ይስጠው። ምግብ ያለውም ለሌለው ያካፍል። መምህር ሆይ እኛ ቀራጮች ነን። ምን እናድርግ? በህግ ከተወሰነላችሁ በላይ አትውሰዱ እኛስ? ምንድን ነው ማድረግ ያለብን? የማንንም ሰው ገንዘብ በግፍ አትቀሙ ማንንም ሰው በሃስት አትወንጅሉ ይላችሁ ብቻ ይብቃችሁ እስቲ ንገረን ... አንተ ክርስቶስ ነህ? እኔ የማጠምቃችሁ በውኃ ነው። ነገር ግን አብዝቶ የሚበልጠኝ ከኔ በኋላ የመጣል። የጫማውን ጠፍር እፈታ ዘንድ እንኳ የማይገባኝ፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል፤ መንሹ በእጁ ነው። የእውድማውንም እህል ያጠራል። ስንዴውንም በጎተራው ይሰበስባል። ህዝቡ ሁሉ ከተጠመቁ በኋላ ጌታ ኢየሱስም ተጠመቀ። ከዚያም እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል በርሱ ላይ ወረደ። ከሰማይም በመጣ ድምጽ "የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፤ በአንተም ደስ ይለኛል" አለ። ኢየሱስም አገልግሎቱን ሲጀምር እድሜው ሰላሳ ያህል ነበር፡፡ መንፈስ ቅዱስን ተሞልቶ ከዮርዳኖስ ተመለሰ፡፡ በመንፈስም ተመርቶ በምድረ በዳ አርባ ቀን በዲያቢሎስ ተፈተነ፡፡ በነዚያ ቀኖች ምንም አልበላም ነበር፡፡ ዲያቢሎስም ሲፈትነው አንተ የእግዚአብሄር ልጅ ከሆንክ፣ ይህን ድንጋይ እንጀራ እንዲሆን እዘዝ በመጽሐፍ ሰው በእግዚአብሔር ቃል እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፏል ከዚያም ዲያቢሎስ ወደ ረጅም ተራራ ወስዶት የአለምን መንግስታት በቅፅበት አሳየው፡፡ ይህ ሁሉ ሃይልና ሃብት ለእኔ ተሰጥቶኛል፤ ለምወደውም ሁሉ መስጠት እችላለሁ። ብታመልከኝ ብትሰግድልኝ ይህንን ሁሉ ሃይልና ሃብትእሰጥሃለሁ። "ለእግዚአብሔር አምላክህ ብቻ ስገድ ... ... እርሱንም ብቻ አምልክ፡፡" ተብሎ ተፅፏል። ከዚያም ዲያቢሎስ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰደው፡፡ በመቅደስም ጨፍ ላይ አቆመውና ይጠብቁህ ዘንድ መላዕክትን ስለአንተ ያዝልሀል፡፡ እግርህም በድንጋይ ከቶ እንዳይሰናከል በእጃቸው ያነሱሀል ተብሎ ተፅፎአልና፣የእግዚአብሄር ልጅ ከሆንክ እስኪ ራስህን ወደታች ወርውር፡፡ በእግዚአብሄር ቃል "ጌታ አምላክህን አትፈታተነው" ይላል። ከዚያም ወዳደገበት ወደ ናዝሬት ተመልሶ መጣ፡፡ ሠላም ሠላም በሰንበትም እንደተለመደው ወደ ምኩራብ ሄደ፡፡ በዚያም ከነቢዩ ኢሳያስ መፅሀፍ ውስጥ ያነብ ዘንድ ሰጡት፡፡ የጌታ መንፈስ በኔ ላይ ነው፡፡ ወንጌልን ለድሆች እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፡፡ ለታሰሩት መፈታትን፣ ለዕውሮች ማየትን፣ አውጅ ዘንድ ልኮኛል፡፡ የተጠቁትን ነፃ አወጣ ዘንድ፤ የተወደደችውን የጌታን አመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል፡፡ እንዴት ድንቅ ነው! የዚህ መፅሀፍ ቃል ዛሬ በጆሮአችሁ እንደሰማችሁት ቃሉ ዛሬ ተፈፀመ! ይህን ተስፋ የሚፈፅመው መሲሁ ብቻ ነው፡፡ ይህን እንዴት እናውቃለን? ያለጥርጥር ምሳሌን በኔ ላይ ትመስሉብኛላችሁ፡፡ ሀኪም ሆይ ራስህን አድን፡፡ እንዲህ ትሉኛላችሁ በቅፍርናሆም ከተማ ያደረከውን ነገር በገዛ አገርህም አድርግ፡፡ እውነት እላችኋለሁ፡፡ ነብይ በገዛ ሀገሩ አይከበርም፡፡ ኢየሱስም እንዲህ እያለ እግዚአብሄር ህዝቡን ያድን ዘንድ እርሱን ቀብቶ የላከው መሲህ እንደሆነ ገለፀላቸው፡፡ አይሁዶች ግን እርሱን እንደመሲህ አልተቀበሉትም፡፡ ከገደል አፋፍ ላይ ወስደው ሊጥሉትም ፈለጉ፡፡ እርሱ ግን በመከከላቸው፤ በመካከላቸውም አልፎ ሄደ በዚያም በገሊላ ከተማ ወደሆነች ወደ ቅፍርናሆም መጣ፡፡ ሮማውያን መጥተው የአይሁዶችን ሀገርና ወገኖቻቸውን በወረራ ስለወሰዱባቸው፤ መሲሁ ነፃ ያወጣናል ብለው በተስፋ ይጠብቁ ነበር፡፡ ሠላም ለእናንተ ይሁን፡፡ ሠላም ላንተ ይሁን ጌታ ሆይ፡፡ ስምዖን፤ ጀልባህን ጥቂት ፈቀቅ ታደርግልኛለህ? እንዴታ? ሊሄድ አይደለም ምቼም ጌታ ሆይ አስተምረን፡፡ አስተምረን፡፡ ኢየሱስ ሆይ አስተምረን፡፡ ይፀልዩ ዘንድ ሁለት ሰዎች ወደ ቤተ መቅደስ ሄዱ፡፡ አንዱ ፈሪሳዊ ሌላው ደግሞ ቀራጭ ነበር፡፡ ፈሪሳዊው ቆመና እንዲህ ብሎ ፀለየ፡፡ አቤቱ እንደ ሌሎቹ ሰዎች እንደ ቀራጮችና እንደ አመፀኞች በተለይም እንደዚህ ቀራጭም ስላላደረከኝ በጣም አመሰግንሀለሁ፡፡ በሳምንት ሁለቴ እፆማለሁ ከማገኘው፣ አስራት አመጣለሁ ብሎ ፀለየ፡፡ ቀራጩ ግን በሩቅ ቆሞ አይኖቹን ወደ ሰማይ ሊያነሳ እንኳን አልወደደም፡፡ ግን ደረቱን እየደቃ፤ አምላኬ ሆይ እኔን ሀጢያተኛውን ማረኝ አለ፡፡ እውነት እላችኋለሁ ከፈሪሳዊው ይልቅ ይሄኛው ፃድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ዝቅ ዝቅ ይላል፡፡ ራሱን የሚያዋርድ ግን ከፍ ከፍ ይላል፡፡ እስቲ ወደ ጥልቁ ባህር ፈቀቅ በል፡፡ በዚያም መረቦቻችሁን አሳ ለማጥመድ ጣሉ፡፡ ጌታ ሆይ! ሌሊቱን ሙሉ ስንለፋ አደርን ግን ምንም አልያዝንም፡፡ ግን አንተ ካልክ፤ መረቡን በስምህ እጥላለሁ፣ ያዕቆብ ዮሀንስ ይበቃል ይበቃል ጌታ ሆይ ከኔ ራቅ፡፡ እኔ ሀጢያተኛ ነኝ፡፡ አትፍራ፡፡ ከአሁን በኋላ ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህ፡፡ ወደ እኔ ኑ፤ ቃሌንም አድምጡ፤ ጆሮአችሁን አዘንብሉ፤ በህይወት ትኖራላችሁ። እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት ቀርቦም ሳለ ጥሩት። ክፉ ሰው መንገዱን፣ በደለኛም ሀሳቡን ይተው፤ ወደ እግዚአብሔር ይመለስ፡፡ ርህራሄው በሱ ላይ ነውና፡፡ ምህረቱም ብዙ ነውና። በደስታ ትወጣላችሁ በሠላም ትጓዛላችሁ፡፡ ተመልከቱ! ወደዚህ እየመጣ ነው። እዚህ ነው። ኢየሱስ ሆይ! ኢየሱስ ሆይ! እባክህ አንዷን ልጄን ማርልኝ ጌታ ሆይ እባክህ ራራልኝ ገና 12 ዓመቷ ነው ልትሞትብኝ ነው። እባክህ ከእኔ ጋራ እንሂድ! ኢያኢሮስ በቃህ ኢየሱስ ሆይ! ልጅህ ሞታለች መምህሩን አታድክመው። አይዞህ አትፍራ እመን እንጂ እሷ ትድናለች አታልቅሱ እሷ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም አንቺ ልጅ ተነሽ የምትበላውን ነገር ስጧት ተጠንቀቁ ይህንን ለማንም እንዳትነግሩ፡፡ ከዚህም በኋላ ሌዊ የተባለው ማቴዎስ ቀረጥ ሰብሳቢ በቀረጥ መሰብሰቢያው ላይ ተቀምጦ አየው፡፡ ተከተለኝ፡፡ ኢየሱስ ይፀልይ ዘንድ ወደ ተራራ ወጣ፡፡ ለሊቱን በሙሉ ወደ እግዚአብሄር ሲፀልይ አደረ፡፡ ሲነጋም ደቀ መዛሙርቱን ጠራ፡፡ አስራ ሁለቱን መረጠ፡፡ ሃዋርያት ብሎ ሰየማቸው፡፡ ጴጥሮስ የተባለው ስምዖን….. ወንድሙ እንድሪያስ…. የያዕቆብ…. ዮሀንስም…. ፊሊሞን…. በርጠለሚዎስም…. ማቴዎስም….. ቶማስ….. የዕልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ…. ቀናተኛው ስምኦን…. የያዕቆብ ወንድም ይሁዳም…. አሳልፎ የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ፡፡ እናንተ ድሆች ብፁዐን ናችሁ፡፡ መንግስተ ሰማያት የእናንተ ናትና፡፡ እናንተ የምትራቡ ብፁዐን ናችሁ፡፡ ትጠጋባላችሁና፡፡ ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ሲጠሏችሁና ሲተዋችሁ ብፁዐን ናችሁ … ስለ ሰው ልጅ ሲነቅፉአችሁና ስማችሁን በክፉ ሲያነሱ ብፁዐን ናችሁ... በዚያ ቀን ይህ ሲሆን ሀሴት አድርጉ፤…. ዋጋችሁ በሰማይ እጅግ ታላቅ ነውና፡፡ አባቶቻችሁም ነቢያትን ልክ እንዲህ ያደርጉባቸው ነበር፡፡ አስራ ሰባት አስራ ስምንት አስራ ዘጠኝ ሀያ... ይህ ብቻ ነው፡፡ እንዲህ ስትል ምን ለማለት ፈልገህ ነው? ነገር ግን እናንተ ባለጠጎች ወዮላችሁ መፅናናታችሁን ተቀብላችኋልና፡፡ እብድ ሳይሆን አይቀርም ባለጠግነትን ንቋል እናንተ አሁን የምትስቁ ወዮላችሁ ታለቅሳላችሁና። ሰዎች ሲያሞግሷችሁ ወዮላችሁ አባቶቻችሁም ለሃሰተኛ ነቢያት እንዲሁ ያደርጉላቸውነበር ለምትሰሙ እውነት እላችኋለሁ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፡፡ ለሚጠሏችሁ መልካም አድርጉ የሚረግሟችሁን መርቁ ለሚበድሏችሁም ሰዎች ፀልዩ ማንም አንደኛውን ጉንጭህን ቢመታህ ሌላውንም ደግሞ አዙረህ ስጠው መጎናፀፊያህንም ለሚወስድ፥ እጀ ጠባብህን አትከልክለው ለሚለምንህ ሁሉ ቸርነትን አድርግ ማንም ያንተን ነገር ቢወስድብህ እንዲመልስልህ አትጠይቀው፡፡ ለሌሎች ሊያደርጉልህ የምትፈልገውን አንተም እንዲሁ ለሌሎች አድርግ የሚወዷችሁን ሰዎች ብቻ ብትወዱ እንዴት ምስጋና ይኖራችኋል? ሀጢያተኞችም እንኳን የሚወዷቸውን ይወዳሉ፡፡ መልካም ለሚያደርጉላችሁ ብቻ መልካም ብታደርጉ፤ እንዴት ምስጋና ይኖራችኋል? ሀጢያተኞችም ያደርጋሉ፡፡ እንዴት ይነካታል? እንዴት ያናግራታል? አስጸያፊ ነው፡፡ ከቶም ጠላቶቻችሁን ውደዱ፡፡ መልካምም አድርጉላቸው፡፡ ምንም ተስፋ ሳታደርጉ አበድሩ፡፡ ያኔ ዋጋችሁ እጅግ ታላቅይሆናል፡፡ የልዑል እግዚአብሄር ልጆች ትሆናላችሁ፡፡ እሱ ለማያመሰግኑትና ለክፉዎችም ቸር ነው፡፡ አባታችሁ ሩህሩህ እንደሆነ፤ እናንተም ሩህሩህ ሁኑ፡፡ ኢየሱስ ሆይ፤ አድነን! እንዳይፈረድባችሁ እናንተም አትፍረዱ፡፡ እንዳትኮነኑ፣…. እናንተም ማንንም አትኮንኑ፡፡ ይቅር በሉ፡፡ እናንተም ይቅር ትባላላችሁ፡፡ ጌታ ሆይ! መንገድህን አሳየን፡፡ ስጡ፡፡ ለእናንተም ይሰጣችኋል፡፡ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ለእናንተም መልሶ ይሰፈርላችኋል፡፡ ዕውር ዕውርን ይመራ ዘንድ አይችልም፡፡ ምክንያቱም ሁለቱም በጉድጓድ ይወድቃሉ፡፡ በራስህ አይን ውስጥ ያለውን ግንድ ሳታይ በወንድምህ አይን ያለውን ጉድፍ ለምን ታያለህ? ጌታ ሆይ! ምራን፡፡ ጌታ ሆይ! አንተን እንሻለን፡፡ የተሸከመችህ ማህፀን የጠባሀቸው ጡቶች ብፁዐን ናቸው፡፡ አዎ ብፁዐንስ የእግዚአብሄርን ቃል የሚሰሙና የሚጠብቁት ናቸው፡፡ ይህንን ሰው ማወቅ አለብኝ፡፡ ለመሆኑ ይህ ሰው መሲሁን ይመስልሃል? አንድ ፈሪሳዊ ኢየሱስን እራት ይበላ ዘንድ ጋበዘው፡፡ እርሱም ፈቅዶ በቤቱ ገብቶ ተቀመጠ፡፡ ልጆች ወደዚያ ሂዱና ተጫወቱ፡፡ ትሰሙኛላችሁ? ሂዱ ተንኮለኞች ናቸው፤ ይሁን እንጂ መልካም ልጆች ናቸው። ደሞ ከዚህ ምን ትሰራለች? እኔ እንጃ…. ምን እያደረገች ነው? እርግጥም ይህ ሰው ነብይ ቢሆን ኖሮ፣ ይህች የምትነካው ሴት ማን መሆኗን ባወቀ ነበር፡፡ ምን አይነት ሀጢያተኛ እንደሆነች በተረዳ ነበር፡፡ ስምዖን ሆይ! ይህች ሴት ማን እንደሆነች አውቃለሁ እስቲ አንድ ነገር ልንገርህ፡፡ ከአበዳሪ ዘንድ ገንዘብ የተበደሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ፡፡ አንደኛው 500 ብር ሌላው 50 ተበደረ፡፡ ሁለቱም የተበደሩትን መመለስ አልቻሉም፡፡ ባለቤቱም የሁለቱንም እዳ ተወላቸው፡፡ ታዲያ የትኛው ነው ይበልጥ የሚወደው? እኔ እንደሚመስለኝ ብዙ ይቅር ያለው ሰው የሚወደው ይመስለኛል፡፡ ትክክል ነክ፡፡ ይህችን ሴት አይተሀታል? አንተ ለእግሮቼ ውሀ እንኳን አላቀረብክልኝም፡፡ እሷ ግን እግሮቼን በእንባዋ አጠበች፤ በፀጉርዋም አበሰችው፡፡ አንተ ጉንጬን እንኳን አልሳምክም፡፡ እሷ ግን ከመጣች ጀምሮ እግሮቼን ከመሳም አላቋረጠችም፡፡ አንተ ለራሴ የወይራ ዘይት አልሰጠኽኝም፡፡ እሷግን እግሮቼን በውድ ሽቶ እያበሰች ነው፡፡ እውነት እልሀለሁ፤ እንዲህ የምታሳየው ታላቅ ፍቅር ብዙ ሀጢያቷ ይቅር እንደተባለላት ያሳያል፡፡ ትንሽ ይቅር የተባለ ሰው ትንሽ ፍቅር ብቻ ያሳያል፡፡ ልጄ ሆይ ኃጢያትሽ ተሰርዮልሻል እምነትሽ አድኖሻልና በሰላም ሂጂ ከዚህም በኋላ ኢየሱስ እየሰበከና ስለ እግዚአብሔር መንግስት የምስራች እየተናገረ ይጓዝ ነበር። ደቀመዛሙርቱና ከክፉ መናፍስት የተፈወሱ ሴቶችም ከእርሱ ጋር ነበሩ... ከእነርሱም መካከል መግደላዊት የተባለችው ማርያም የሄሮድስ አዛዥ የኩዛ ሚስት ዮሓናም ሶስናም በገሊላ የሮማ እንደራሴ ሆኖ ይገዛ የነበረው ሄሮድስ፥ የወንድሙን ሚስት በማግባቱ ስለገሰፀው ዮሐንስ መጥምቁን ወደ እስር ቤት ጣለው እሺ! በማግስቱም አንዲት ናይን ወደምትባል ከተማ ደረስን፡፡ እነሆ የሞተ ሰው ለመቅበር ተሸክመውት ነበር ሟቹም ለእናቱ አንድ ልጅ ብቻ ነበር፡፡ የሟቹን እናት ጌታም ባየ ጊዜ ልቡ በሀዘን ተነካ ራራላትም፡፡ ቀርቦም ቃሬዛውን ነካና "አንተ ጎበዝ እልሀለሁ ተነስ፤ አለው፡፡" ሞቶ የነበረው ሰው ቀና ብሎ ተቀመጠ ኢየሱስም ልጁን ለእናቱ መልሶ ሰጣት፡፡ ጠይቁት ተናገር ዮሀንስ ይመጣል ያለው አንተ ነህን? ወይስ ሌለ ሰው እንጠብቅ? ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ መጥምቁ ዮሀንስ እንጠይቅህ ዘንድ ላከን፡፡ ይመጣል የተባልከው መሲህ አንተ ነህን? ወይስ ሌላውን እንጠብቅ ብሎሀል፡፡ ሂዱና ለዮሐንስ ያያችሁትን ንገሩት እውሮች ያያሉ አንካሶችም ይዘላሉ በኔ የማይሰናከለው ምንኛ ብፁዕ ነው። ወደ ላይ አንሳኝ ትከሻዬ ላይ ሁን፥ ይታይሃል? ኢየሱስን ማየት ቻልኩ! ገበሬ ዘር ተሸክሞ ሊዘራ ወጣ። ሲዘራም አንዳንዱ ዘር በመገድ ዳር ወደቀ ተረገጠም የሰማይ ወፎችም መጥተው በሉት። ሌላውም ዘር በዓለት ላይ ወደቀ የተዘራውም ዘር በበቀለ ጊዜ መሬቱ እርጥበት ስላልነበረው ደረቀ። ሌላውም ዘር በእሾህ መካከል ወደቀ እሾሁም ከዘሩ ጋር አብሮት በቀለ ከዚያም አነቀው ሌላውም ዘር በመልካም መሬት ላይ ወደቀ በበቀለም ጊዜ እጅግ መልካም ሆነ አንዳንዱም 100 እጥፍ አፈራ ጌታ ሆይ! ህዝብ በሚሰበሰብበት ጊዜ ሁሉ በምሳሌ የምትናገረው ስለምንድ ነው? ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግስት ሚስጥር ለማወቅ ተሰጥቶአችኋል፡፡ ሌሎች ግን እያዩ እንዳይመለከቱ የግድ በምሳሌ ይነገራቸዋል፡፡ እየሰሙ የማያስተውሉ ስለሆኑ ነው፡፡ የምሳሌውም ትርጉም ይህ ነው፡፡ ዘሩ የእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ እነዚህ በመንገድ ዳር ላይ የወደቁት ዘሮች ቃሉን የሚሰሙት ብቻ ናቸው፡፡ ነገር ግን ዲያቢሎስ ይመጣል አምነውም እንዳይድኑ ቃሉን ከልባቸው ይወስዳል፡፡ በአለት ላይም የወደቁት ዘሮች ሲሰሙ ቃሉን በደስታ የሚቀበሉ ሰዎች ናቸው፡፡ ለጊዜው ነው እንጂ ሥር የላቸውም፡፡ የሚያምኑት ለጊዜው ነው፡፡ ፈተናና መከራ በመጣ ጊዜ ግን፣ ሁሉም ፈርተው ይክዳሉ፡፡ እነዚህ በእሾክ መካከል የወደቁት ዘሮች ቃሉን የሚሰሙት ናቸው፡፡ ነገር ግን በህይወታቸው ዘመን ስለራሳቸው በማሰብና በብልጥግናቸውና በምኞታቸው ይታነቃሉ፡፡ ስለዚህ ሙሉ ፍሬ አያፈሩም፡፡ እነዚህ በመልካም መሬት ላይ የወደቁት ዘርች ደግሞ፤ እነርሱ በመልካምና በበጎ ልብ የቃሉን መልዕክት ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው፡፡ በህይወታቸውም ሙሉ ፍሬን የሚያፈሩ ናቸው፡፡ ማንም መብራትን አብርቶ በእንቅብ የሚከድነው ወይም ከአልጋ በታች የሚያኖረውም የለም፡፡ ከዛ ይልቅ በመቅረዝ ያኖረዋል፡፡ ስለዚህ ሰዎች ወደ ውስጥ ሲገቡ መብራቱን በግልጥ ያዩታል፡፡ የማይገለጥና የተሰወረ የለም፡፡ ወደ ግልጥም የማይወጣ የሚደበቅና የተሸሸገ ምንም አይነት ነገር ሊኖር አይችልም፡፡ እንግዲህ እንዴት እንድትሰሙ ተጠበቁ፡፡ ምክንያቱም ላለው ሰው ይሰጠዋልና፡፡ ከሌለው ግን ያው ያለው የሚመስለው እንኳ ይወሰድበታል፡፡ መምህር ሆይ! እናትህና ወንድሞችህ ከውጭ ቆመዋል ሊያዩህ ይፈልጋሉ፡፡ እናትና ወንድሞቼ የእግዚአብሄርን ቃል የሚሰሙና፤ የሚታዘዙም ናቸው፡፡ አንድ ቀን ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ታንኳ ገብቶ "ወደ ማዶ እንሻገር" አላቸው፡ እነርሱም ተነሱ፣ ሲሄዱም ሳለ እርሱ አንቀላፋ፡፡ ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! ኢየሱስ ሆይ! እባክህ ማለቃችን ነው፡፡ ማዕበሉ እያናወጠን ነው፡፡ መጥፋታችን ነው፡፡ ጌታ ሆይ አድነን፡፡ ማዕበል የሚታዘዝለት ይህ ማነው? እምነታችሁ ወዴት አለ? ከዚያም በኋላ ከገሊላ አንፃር ወዳለችው ወደ ጌርጌሲኖስ አገር በታንኳ ደረሰ፡፡ ኢየሱስ ሆይ! የልዑል እግዚአብሄር ልጅ ሆይ! እኔ ከአንተ ምን አለኝ? እባክህ አታሰቃየኝ፡፡ ማን ትባላለህ? ለጊዮን ጌታ ሆይ! እንለምንሀለን እባክህ ወደ ጥልቁ አትጣለን፡፡ ወደ አሳማዎቹ መንጋዎች ሄደን እንግባ እናንተ አትመለሱም፡፡ ቁሙ! ተመለስ! አጋንንትም ከሰውየው ላይ ወጥተው ወደ እርያዎች ገቡ፡፡ ከዚህ ሂድልን፡፡ አንተ አስማተኛ ሂድልን፡፡ ከዚህ ቦታ ሂድልን ሂድ ጥፋ ሂድ ከዚህ ጥፍ፡፡ ወደ ምትሄድበት ሁሉ እከተልሀለው፡፡ እባክህ ፍቀድልኝ ካንተ ጋር ልምጣ ወደ ቤትህ ተመለስና እግዚአብሄር ያደረገልህን ተናገር፡፡ ጌታ ሆይ! ህዝቡን ሸኛቸው፡፡ በዙሪያችን ወዳሉት መንደሮችና ገጠሮች መሄድ ይችላሉ፡፡ በዚያም ማደሪያና ምግባቸውን ይፈልጉ፡፡ እናንተ ራሳችሁ የሚበሉትን ስጧቸው፡፡ ያለን አምስት ዳቦና ሁለት አሳ ብቻ እኮነው፡፡ አንተ የተባረክህ! ጌታ አምላካችን ሆይ! የዓለማት ሁሉ ንጉስ፤ ከምድር መብልን የምትሰጥ አንተነህ። ድንቅ ነው የማይታመን ነው! ህዝቡ እኔን ማን ይሉኛል? አንዳንዶች መጥምቁ ዮሀንስ ነህ ይሉሀል፡፡ ሌሎች ደግሞ ኤሊያስ ነህ ይላሉ፡፡ ለሌሎች ደግሞ ከቀደሙት ነቢያት መካከል አንዱ፤ ተነስቷል ይላሉ፡፡ እናንተስ እኔን ማን ትሉኛላችሁ? አንተ የእግዚአብሔር መሲህ ነህ። ይህንን ለማንም እንዳትነግሩ፡፡ የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበልና ሊጣል፣ እንዲሁም ሊገደል በሶስተኛውም ቀን ሊነሳ ይገባዋል፡፡ ከእናንተ መካከል እኔን ሊከተል የሚወድ ይኖራልን? ጌታ ሆይ እኔ እከተልሀለሁ፡፡ ግን አስቀድሜ፤ ወደ ቤቴ ሄጄ፤ ቤተሰቦቼን እንድሰናበት ፍቀድልኝ፡፡ ማንም እርፍ ጨብጦ ወደ ኋላ የሚመለስ ቢኖር ለእግዚአብሄር መንግስት የተገባ አይደለም፡፡ ማንም በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ፡፡ መስቀሉንም ተሸክሞ ዕለት ዕለት ይከተለኝ፡፡ ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ያጠፋታል፣ ስለ እኔ ሲል ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ እርሱ ያድናታል፡፡ ሰው አለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል? ማንም በእኔና በቃሌ የሚያፍር ቢኖር፤ በአባቱና በቅዱሳን መካከል፡፡ የሰው ልጅ በክብሩ በተገለጠ ጊዜ እርሱም ያፍርበታል፡፡ እውነት እልሀለሁ፤ የእግዚአብሔርን መንግስት እስኪያዩ ድረስ ሞትን የማይቀምሱ አንዳንዶች እዚህ አሉ፡፡ ከዚያም ኢየሱስ፣ ዮሀንስን፣ ያዕቆብንና ጴጥሮስን ይዞ ይፀልይ ዘንድ ወደ ተራራ ወጣ፡፡ ሲፀልይም ሳለ የፊቱ መልክ ተለወጠ፣ ልብሱም ተብለጭልጮ ነጭ ሆነ፡፡ ወዲያውኑ እነሆ ሁለት ሰዎች ከእርሱ ጋር ነበሩ፤ እነርሱም ሙሴና ኤሊያስ ከሰማይ በክብር መጥተው ይነጋገሩ ነበር፡፡ የእግዚአብሄርን አላማ ትፈፅማለህ፡፡ በኢየሩሳሌም ትሞታለህ፡፡ ከእነርሱ ሲለይ ጴጥሮስም እየሱስን አለው አቤቱ ጌታ ሆይ በዚህ መሆን ለኛ መልካም ነው፡፡ ሶስት ድንኳኖችን እንሰራለን፡፡ አንድ ለአንተ... ይህንንም ሲናገሩ ደመና መጣና ጋረዳቸው ወደ ደመናውም ሲገቡ ሳለ ፈሩ ከደመናውም የመረጥኩት ልጄ ይህ ነው፡፡ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ፡፡ መምህር ሆይ! መምህር ሆይ! ልጄን እንድታድንልኝ እለምንሀለው፡፡ እባክህ እባክህ ጌታ ሆይ፤ እርዳልኝ ያለኝ ልጅ እርሱ ብቻ ነው፡፡ ደቀ መዛሙርትህንም አጋንንቱን ያስወጡለት ዘንድ ለመንኳቸው፡፡ እነርሱ ግን አልቻሉም፡፡ አንተ የማታምን ጠማማ ትውልድ እስከ መቼ ድረስ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? ልጅህን ወዲህ አምጣ፡፡ ፊቱ እንኳን ሳይቀር ተፈወሰ፡፡ እንዴት ይገርማል ዮሀንስ ለደቀመዛሙርቱ እንዳስተማረ እንዴት እንደምንፀልይ አስተምረን፡፡ ስትፀልዩ እንዲህ በሉ፡፡ በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ ስምህ ይቀደስ መንግስትህ ትምጣ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን፡፡ የዕለት እንጀራችንን ስጠን፡፡ የበደሉንን ይቅር እንደምንል፡፡ በደላችንን ይቅር በለን፡፡ ወደፈተናም አታግባን፡፡ ከክፉ ሁሉ አድነን እንጂ፡፡ ለምኑ ይሰጣችሁማል፡፡ ፈልጉ ታገኙማላችሁ፡፡ መዝጊያን አንኳኩ ይከፈትላችሁማል፡፡ የሚለምን ሁሉ ይቀበላልና፡፡ የሚፈልግ ደግሞ ያገኛል፡፡ መዝጊያን ለሚያንኳኳ ሁሉ ይከፈትለታል፡፡ ከእናንተ መካከል ልጆቻችሁ ዓሳ ቢለምኗችሁ እባብን እንቁላል ቢለምኗችሁ ጊንጥን ትሰጣላችሁን? ታዲያ ክፉዎች ሆናችሁ ለልጆቻችሁ መልካም መስጠትን ካወቃችሁ በሰማይ ያለው አባት ለሚለምኑት ቅዱስን መንፈስ እንዴት አብልጦ አይሰጣቸው? እውነት እላችኋለው፤ ለነፍሳችሁ ስለምትበሉት ነገር አታስቡ ለሰውነታችሁ ስለምትለብሱት ነገር አትጨነቁ፡፡ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ ይበልጣል ቁራዎችን ተመልከቱ፡፡ አይዘሩም አያጭዱምም ማከማቻ ወይም ጎተራም የላቸውም፡፡ እግዚአብሔር ግን ይመግባቸዋል፡፡ ታዲያ እናንተ ከወፎች ምንኛ ትበልጣላችሁ? ከእናንተ ማንም ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማነው? እንግዲህ ትንሹን ነገር ስንኳ የማትችሉ ከሆናችሁ፣ ስለምን በሌላ ነገር ትጨነቃላችሁ? አበቦችን ተመልከቱ ፡፡ እንዴት እንደሚያድጉ፣ አይደክሙም፣ አይፈትሉምም፡፡ ሰለሞን እንኳ ከክብሩ ከነዚህ እንደ አንዲቱ አልለበሰም፡፡ እግዚአብሄር ግን፣ ዛሬ ታይቶ ነገ ደግሞ የሚደርቀውን የሜዳ ሳር እንዲህ ካስዋበ እናንተንማ ይልቁን እንዴት እናንተ እምነት የጎደላችሁ፡፡ ጌታ ሆይ! እምነት ጨምርልን፡፡ የሰናፍጭ ቅንጣት የምታህል ዕምነት ቢኖራችሁ፣ ይህንን የሾላ ዛፍ ተነቅለህ፣ ወደ ባህር ተተከል ብትሉት በሚገባ ይታዘዛችሁ ነበር፡፡ መሰናክል ግድ ሳይመጣል አይቀርም፡፡ ነገር ግን መሰናክሉን ለሚያመጣው ወዮለት፡፡ ስለዚህ ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ከሚያሰናክል ይልቅ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባህር ቢጣል ይሻለው ነበር፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት ምን ትመስላለች? ይህን ትመስላለች፡፡ ሰው ወስዶ በአትክልት ሥፍራ የጣላትን የሳንፍጭ ቅንጣት ትመስላለች፡፡ ተክሏም አደገች ታላቅም ዛፍ ሆነች፡፡ የሰማይ ወፎችም በቅርንጫፎችዋ ሰፈሩ፡፡ ስለ ምን እንደሚናገር አልገባኝም፡፡ ስለ ምን ከቀራጮችና ኃጢያተኞች ጋር ትበላላችሁ? ጤነኞች ባለ መድሀኒት አያስፈልጋቸውም ህመምተኞች ግን ያሻቸዋል፡፡ እኔ ፃድቃንን ወደ ንስሃ ልጠራ አልመጣሁም፡፡ ሀጢያተኞችን እንጂ፡፡ ስለ እግዚአብሄር መንግስት ደግመህ ንገረን፡፡ ሌላስ ትነግረናለህን? አንተ ታናሽ መንጋ መንግስትን ሊሰጣችሁ ያባታችሁ በጎ ፈቃድ ነውና አትፍሩ፡፡ ያላችሁን ሽጡ ምፅዋትም ስጡ፡፡ ያላችሁ መጽዋትም ስጦታ ሌባ በማይደፍረው በማይጠፋው በሰማያት መዝገባ ኑሩ መዝገባችሁ ባለበት ልባቸው ይሆናል ምክንያቱም ሌባ በማይቀርብበት፡፡ ከስሞ ደግሞ በማይጠፋበት፡፡ መዝገባችሁ ባለበት ልባችሁ ደግሞ በዚያ ይሆናልና፡፡ አንቺ ሴት ከህመምሽ ተፈውሰሻል፡፡ ተመልከት ዳነች ድንቅ ነው፡፡ እይ ተፈወሰች ናና እይ፡፡ ጌ--ጌ---ጌታ የተመሰገነ ይሁን፡፡ አስራ ስምንት አመት መምህር ሆይ ተመስገን፡፡ ልንሰራባቸው የሚገቡን ስድስት ቀኖች አሉን፡፡ እንግዲህ በእነርሱ መጥታችሁ ተፈወሱ እንጂ፤ በሰንበት ቀን አይደለም፡፡ እናንተ ግብዞች! ከእነናንተ እያንዳንዱ በሰንበት በሬውን ወይስ አህያውን ከግርግሙ ፈቶ ውሃ ሊያጠጣው ይወስደው የለምን? ይህችም የአብርሀም ልጅ ሆና ከአስራ ስምንት አመት ጀምሮ ሰይጣን ያሰራት ነበረች፡፡ ታዲያ በሰንበት ቀን ከዚህ ዕስራት ልትፈታ አይገባትምን? ቸር መምህር ሆይ፤ የዘላለም ህይወት አገኝ ዘንድ ምን ላድርግ? ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሄር በቀር ቸር ማንም የለም፡፡ ትእዛዛቱን አንተ ታውቃቸዋለህ ከቶም አታመንዝር ከቶም አትግደል በሀሰትም አትመስክር፡፡ እናትና አባትህንም አክብር ይህን ሁሉ ከህፃንነቴ ጀምሮ ጠብቄአለሁ፡፡ አሁንም አንዲት ነገር ገና ቀርታሀለች ያለህን ሁሉ ሽጠህ ለድሆች ስጥ በሰማይም መዝገብ ታገኛለህ መጥተህም ተከተለኝ፡፡ ታዲያ እኛ ነጋዴዎች ነን፡፡ ሀብታሞች ነን፡፡ ገንዘብ ላላቸው ወደ እግዚአብሄር መንግስት መግባት እንዴት ጭንቅ ነው፡፡ ባለጠጋ ወደ እግዚአብሄር መንግስት ከሚገባ ይልቅ፤ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል፡፡ ታዲያ ማን ሊድን ይችላል? ለሰው የማይቻለው ሁሉ ለእግዚአብሔር ግን ይቻላል፡፡ ታዲያ የእግዚአብሄር መንግስት መቼ ትመጣለች? የእግዚአብሄር መንግስት ከቶም በመጠባበቅ አትመጣም፡፡ ማንም ሰው እንኋት፤ በዚህ ወይም በዚያ አለች ሊል አይችልም፤ የእግዚአብሄር መንግስት በመካከላችሁ ናትና፡፡ ከሰው ልጅ ቀኖች አንዱን ልታዩ የምትመኙበት ወራት እንደሚመጣ ይህን እወቁ፡፡ ነገር ግን አታይዋትም፡፡ መብረቅ በርቆ ከዳር እስከ ዳር እንደሚያበራ የሰው ልጅ በቀኑ እንደዚያ ይሆናል፡፡ አስቀድሞ ግን ብዙ መከራ እንዲቀበል ከዚህም ትውልድ እንዲጣል ይገባዋል፡፡ ነገር ግን ከህግ አንዲት ነጥብ ከምትወድቂልቅ ሰማይና ምድር ቢያልፍ ይቀላል እላችኋለሁና እናንተ የምታዩትን ብዙዎች ነብያትና ነገስታት ሊያዩ ወደዱ አላዩም፡፡ የምትሰሙትንም ሊሰሙ ወደው አልሰሙም፡፡ ምን እናድርግ? በህግ የተፃፈው ምንድነው? እንዴትስ ታነበዋለህ? ጌታ አምላክህን በፍፁም ልብህ በፍፁም ነፍስህ በፍፁም ሀይልህ ሀሳብህም ውደድ፡፡ ባልንጀራህንም እንደራስህ አድርገህ ውደድ፡፡ ትክክል ነህ፡፡ ይህን አድርግ በህይወትም ትኖራለህ ጎረቤቴ ማነው? መቼም እነዚያ ወታደሮች አይሆኑም፡፡ ቄሳርስ ቢሆን? አንድ ጊዜ አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ወረደ፡፡ በወንበዴዎችም እጅ ወደቀ፡፡ እነሱም ገፈፉት፣ ደበደቡትም፣ በህይወትና በሞት መካከል ትተውት ሄዱ ድንገትም አንድ ካህን፣ በዚያ መንገድ ወረደ፣ አይቶትም ገለል ብሎ አለፈ፡፡ እንዲሁም ደግሞ አንድ ሌዋዊ ወደዚያ ስፍራ መጣና አይቶት ገለል ብሎ አለፈ፡፡ አንድ ሳምራዊ ግን ሲሄድ ወደ እርሱ መጣ አይቶትም ልቡ በሀዘን ተነካ፡፡ ቀርቦም ዘይትና የወይን ጠጅ .. በቁስሎቹ ላይ አፍስሶ አሰራቸው፡፡ ከዚያም በርሱ አህያ ላይ አስቀምጦት ወደ እንግዶች ማደሪያ ወሰደው ጠበቀውም፡፡ በማግስቱም ሁለት ዲናር አውጥቶ ለባለቤቱ ሰጠና ጠብቀው ከዚህም በላይ የምትከስረውን ሁሉ እኔ ስመለስ እከፍልሀለው አለው፡፡ እንግዲህ ከእነዚህ ከሶስቱ በወንበዴዎች እጅ ለወደቀው ባልንጀራ የሆነው ማን ይመስልሀል? ቸርነት ያደረገለት ሰው ነው፡፡ ሂድ አንተም እንዲሁ አድርግ፡፡ ኦጵ! ህፃናት ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሉአቸው፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት እንደነዚህ ላሉት ናትና፡፡ እውነት እውነት እላችኋለሁ፡፡ የእግዚአብሄር መንግስት እንደ ህፃን የማይቀበላት ሁሉ፤ ከቶም ወደ እርሷ አይገባባትም፡፡ ማንም እነዚህን ህፃናት በስሜ የሚቀበል፣ እኔን ይቀበላል፡፡ ማንም እኔን የሚቀበል ቢኖር የላክሁትንም ይቀበላል፡፡ ከእናንተ መሀል ታናሽ የሆነ እርሱ ታላቅ ይሆናል፡፡ ሰማኸኝ፣ ይህ የምሰማው ነገር ምንድነው? የናዝሬቱ ኢየሱስ በዚህ በኩል እያለፈ ነው፡፡ ኢየሱስ ሆይ! ኢየሱስ ሆይ! የዳዊት ልጅ ሆይ! እባክህ ማረኝ፡፡ ምን አደርግልህ ዘንድ ትወዳለህ? ማየት እፈልጋለሁ፡፡ እይ! እምነትህም አድኖሀል፡፡ ማየት ቻልኩ! አየሁ! ማየት ቻልኩ! ጌታ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ሲሄድ ብዙ ሰዎች ተሰብስበው የደህንነትን መንገድ እንዲያሳያቸው፣ ስለ እግዚአብሄር መንግስትም እንዲያስተምራቸው ይጠይቄት ነበር፡፡ ይህ ሰው በእውነትም ነብይ ነው፡፡ ጌታዬና አምላኬ ሆይ! አድነኝ፣ ጌታ ሆይ! አድነን! አድነን፡፡ ጌታ ይመስገን፡፡ ጌታ ሆይ እውነተኛውን መንገድ አሳየን፡፡ ህዝቡም ኢየሱስን እንደ አምላክና ጌታ መቀበል ጀመረ፡፡ በኢያሪኮም ዘኪዎስ የሚባል ቀራጭ ባለጠጋ ነበር፡፡ ኢየሱስንም ሊያይ በሾላ ዛፍ ላይ ወጣ፡፡ ያ ቀራጩኮ ነው፡፡ ዘኪዎስ ሆይ ፈጥነህ ውረድ ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛል፡፡ እኔ ቤት ነው? በሱ ቤት ማን ሊገባ የሚወድ አለ? ስሙኝ ካለኝ ሀብት ከፊሉን ለድሆች እሰጣለሁ፡፡ ማንንም በሀሰት ከስሼ እንደሆን አራት እጥፍ እመልሳለሁ፡፡ እኔ አላምንም! ቀራጭ የሰበሰበውን ቀረጥ ሊመልስ ዘንድ ይቻለዋልን? አይመስለኝም እርሱም ደግሞ የአብርሀም ልጅ ነው፣ ዛሬ ለዚህ ቤት መዳን ሆኖለታል፡፡ የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአልና፡፡ ስሙ ስለ ሰው ልጅም በነብያት የተፃፈው ሁሉ ይፈፀም ዘንድ፤ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣ። ለአህዛብም አሳልፈው ይሰጡታል ይዛበቱበታልም ያንገላቱታል ይተፉበታልም፡፡ ይገርፉታል ይገድሉትማል፡፡ በሶስተኛውም ቀን ግን ይነሳል ጌታ ኢየሱስ ስለሰው ልጆች ኃጢአት መሞቱን እያወቀ ወደ ኢየሩሳሌም መንገዱን አቀና ብዙ ህዝብም በመምጣቱ ደስ ብሎት እንደተቀበሉት ደቀመዛሙርትህን ዝም እንዲሉ እዘዛቸው! እውነት እላችኋለሁ እነዚህ ዝም ቢሉ እንኳ ድንገጋዮች ራሳቸው መጮህ ይጀምራሉ ሰላም ክብር ጤንነት! ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ቀርቦ ባያትም ጊዜ አለቀሰላት ለሰላምሽ የሚሆነውን ዛሬ በተረዳሽ ኖሮ! እሁን ግን ከዓይንሽ ተሰውሯል። ጠላቶችሽም ዙሪያሽን ቅጥር ሰርተው ከየአቅጣጫውም ከበው የሚያስጨንቁበት ጊዜ ይመጣልና በቅጥሮቹም ውስጥ ያጥፉሻል፤ የመጎብኘትሽን ዘመን አላወቅሽምና፤ አንቺና ልጆችሽን ወደ ታች ይጥላሉ በአንቺ ውስጥ ድንጋይ በድንጋይ ላይ አይተውም በኢየሩሳሌም የሚገኘው ቤተ መቅደስ ከማምለኪያ ቦታነት ይልቅ የንግድ መናህርያ ሆኖ ነበር፡፡ ቤቴ የፀሎት ቤት ይሆናል ተብሎ ተፅፏል እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት! ከብቶችን ለቀቀብን ያዘው ያዘው! ወታደር ጥራ! ወታደር ጥራ! ዝቡ ሁሉ ኢየሱስን እንደ ንጉስ አድርገው ተቀብለውት ነበርና ከሸንጎ መሪዎች ዘንድ ተቃውሞ እየሰፋ ሄደ ብዙዎች እርሱን እንደ ንጉስ አድርገው እንደ ተቀበሉት ተረድቻለሁ፡፡ ንጉስ? የለማኞች የአመንዝሮችና የቀማኞች ንጉስ። የሱን አይነቶች ከዚህ በፊት ብዙዎችን አይተናል ይመጣሉ ምኞታቸውን ይገልፃሉ ይሄዳሉ፤ ከዚያም ይረሳሉ፡፡ አስተውሉ ተከታዮቹም በየዕለቱ እየጨመሩ ነው ህዝቡ ሁሉ ያደንቁታል ንጉስም እንደሆነ ያስባሉ ማስጠንቀቂያ ልስጣቸሁ። ይህ ሰው ከዚህ በኋላ ዳግመኛ ሰላም ቢነሳ፤ በሀላፊነት እጠይቃችኋለሁ፡፡ ልክ ሳይሆን አይቀርም ያንን ገሊላዊ የምንቋቋምበት ጊዜው አሁን ነው፡፡ ኢየሱስም፤ በየቀኑ አብዛኛው ጸሐፍትና ፈሪሳውያንን ህጉን ይሰብካሉ እንጂ አይፈጽሙትም እያለ ይናገራቸው ነበር። በቤተ መቅደስ ኢየሱስ አንዲት ደሃ መበለት ሁለት ሳንታም በዚያ ስትጥል አየ በጣም ትንሽ ነው የበለጠ መስጠት አትችልም? እውነት እላችኋለው ይህች ደሃ መበለት ከሁሉ ይልቅ አብልጣ ጣለች፡፡ እነዚህ ሁሉ ከትርፋቸው ወደ እግዚአብሄር መዝገብ ጥለዋል፡፡ ይህች ግን ከጉድለቷ የነበራትን ትዳርዋን ሁሉ ጣለች፡፡ እስኪ ንገረን እነዚህን በምን ስልጣን ታደርጋለህ? ስልጣንን የሰጠህ ማነው? እኔ ደግሞ አንዲት ነገር እጠይቃችኋለሁ የዮሀንስ ጥምቀት ከሰማይ ነበረች ወይስ ከሰው? ምን እንበል? ከሰማይ ነው ብንል ስለምን ዮሀንስን አላመናችሁትም ይለናል፡፡ ከሰው ነው ብንል ደግሞ ይህ ሁሉ ህዝብ ይወግረናል፡፡ ዮሀንስ ነብይ እንደነበር ህዝቡ ሁሉ ያምኑ ነበርና፡፡ ከየት እንደመጣ አናውቅም እኔም በምን ስልጣን እነዚህን እንዳደርግ አልነግራችሁም አንድ ሰው የወይን አትክልት ተክሎ ነበር፡፡ ለገበሬዎችም አከራይቶ ለረጅም ጊዜ ቤቱን ትቶ ሄደ የወይን ማፍሪያ ወቅት በደረሰ ጊዜ ከወይን አትክልቱ ፍሬ እንዲሰጡት አንድ ባሪያ ወደ ገበሬዎቹ ላከ፡፡ ገበሬዎቹ ግን ደበደቡት ባዶውንም ሰደዱት ስለዚህ ሌላ በሪያ ላከ፡፡ እነርሱም ያንን ባሪያ ደበደቡት አዋርደውም ወደ ጌታው ላኩት ጨምሮም ሶስተኛውን ላከ እነርሱም ይህንን ደግሞ አቁስለው አወጡት ከዚያም የወይኑ ባለቤት "ምን ላድርግ" አንድ ልጄን ብልክ ይሻላል ምን አልባት እሱን አይተው ያፍሩታል አለ ግን ገበሬዎቹ አይተውት እርስ በእርሳቸው ሲነጋገሩ ወራሹ እርሱ ነውና ርስቱ ለኛ እንዲሆን እንግደለው አሉ፡፡ ጌታ ሆይ ሌላም ንገረን ከወይኑ አትክልት ወደ ውጭ አውጥተው ገደሉት እንግዲህ የወይኑ አትክልት ጌታ ምን ያደርጋቸዋል? አዎ ይመጣል ገበሬዎቹን ያጠፋል የወይኑንም አትክልት ለሌሎች ይሰጣል፡፡ ይህ ቃል ምን ማለት ነው? ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ ከሁሉም በለጠ የማዕዘን ራስም ሆነ በዚያም ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ሁሉ ይቀጠቀጣል የሚወድቅበትን ሁሉ ግን ይፈጨዋል ያደቀዋል፡፡ መምህር ሆይ ያስተማርካቸው ሁሉ እውነት እንደሆነና የሰውንም ፊት አይተ እንዳታደላም እናውቃለን የእግዚአብሄርን እወነት ታስተምራለህ፡፡ እሰቲ ንገረን እንደ ህጋችን ለሮማን ቄሳር ግብር መገበር ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? አንድ ዲናር አሳዩኝ መልኩና ፅህፈቱስ የማነው? የቄሳር እንኪያስ የቄሳር የሆነውን ለቄሳር ስጡ የእግዚአብሄርንም ለእግዚአብሄር አስረክብ ፋሲካንም ሊያደርጉበት የሚገባው የቂጣ በአል ደረሰ፡፡ ጴጥሮስና ዮሀንስንም ፋሲካን እንበላ ዘንድ ሄዳችሁ አዘጋጁን ብሎ ጌታ ላካቸው ከመከራዬ በፊት ለእናንተ ጋር ይህንን ፋሲጋ ልበላ እጅግ እመኝ ነበር እላችኋለሁና የእግዚአብሄር መንግስት እስኪፈፀም ድረስ ወደፊት ከዚህ አልበላም፡፡ አንተ የተባረክህ! ጌታ አምላካችን ሆይ! የዓለማት ሁሉ ንጉስ ከወይን ፍሬን የምትሰጥ አንተነህ። ይህን እንካችሁ በመሀላችሁ ተካፈሉት እላችኋለሁና የእግዚአብሄር መንግስት እስክትመጣ ድረስ ከአሁን ጀምሮ ከወይን ፍሬ አልጠጣም፡፡ አንተ የተባረክህ! ጌታ አምላካችን ሆይ! የዓለማት ሁሉ ንጉስ ከምድር መብልን የምትሰጥ አንተነህ። ይህ ስለእናንተ የሚሰጠው ስጋዬ ነው ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት ይህ ፅዋ ስለ እናንተ ለሚፈሰው ደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው ስሙ፤ አሳልፎ የሚሰጠኝ ሰው እጅ በማእድ ከእኔ ጋር ናት። ምን!? የሰው ልጅ እንደተወሰነው ተላልፎ ይሰጣል፡፡ ነገር ግን አሳልፎ ለሚሰጠው ለዛ ሰው ወዮለት እኔ እሆንን? ማን እንደሆነ ጠይቀው። ጌታ ሆይ ማን ነው? ፈፅሞ አልከዳህም! ከእናንተ ታላቅ የሆነ በመካከላችሁ እንደ ታናሽ ይሁን የሚገዛም እንደሚያገለግል ይሁን በማዕድ የተቀመጠ ወይስ የሚያገለግል የትኛው ነው ታላቅ? የተቀመጠው አይደለምን? እኔ ግን በመካከላችሁ እንደሚያገለግለው ነኝ ነገር ግን እናንተ በፈተናዎቼ ከኔ ጋር ጸንታችሁ የኖራችሁ ናችሁ፡፡ አባቴ እኔን እንደሾመኝ እኔ ደግሞ በመንግስቴ በማዕዴ ትበሉና ትጠጡ ዘንድ እንደዚሁም በአስራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ልትፈርዱ በዙፋኖች ትቀመጣላችሁ፡፡ ስለዚህ ከዳተኛ የለም ማለት ነው ስምዖን ስምዖን ሆይ! ሰይጣን ሁላችሁንም ሊፈትናችሁ ፈለገ፡፡ እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁና ሊፈትናችሁ ለመነ እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ ማለድሁ አንተም ወደ እኔ በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አፅና፡፡ ጌታ ሆይ እኔ ካንተ ጋር ለመታሰርና ለመሞት ዝግጁ ነኝ! ጴጥሮስ ሆይ እልሀለሁ ዛሬ ዶሮ ሳይጮህ አላውቀውም ብለህ ሶስት ጊዜ ትክደኛለህ፡፡ ያለኮሮጆና ያለ ከረጢት ያለ ጫማም በላኳችሁ ጊዜ አንዳች ጎደለባችሁን? በፍፁም ምንም ነገር አሁን ግን ኮሮጆ ያለው ከርሱ ጋር ይውሰድ ከረጢትም ያለው እንዲሁ ሰይፍ የሌለውም ልብሱን ሽጦ ይግዛ እላችኋለሁ ከአመፀኞች ጋር ተቆጠረ ተብሎ በቃሉ የተፃፈው በእኔ ይፈፀም ዘንድ ይገባል፡፡ ተመልከት፤ ጌታ ሆይ! ይኸው ሁለት ሰይፎች አሉን በቂ ነው። የካህናት አለቆችም ኢየሱስን እንዴት አድርገው ማስወገድ እንደሚችሉ ለመምከር ይገናኙ ነበር። ከዚያም፤ ከ12ቱ አንዱ በሆነው በአስቆሮቱ ይሁዳ ውስጥ ሰይጣን ገባበት፡፡ ኢየሱስን አሳልፎ ሊሰጥ ወደ ካህናት አለቆች አመራ፡፡ ኢየሱስም ይፀልይ ዘንድ ከኢየሩሳሌም ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ሄደ ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ፀልዩ የአስቆሮቱ ይሁዳ ጌታ ኢየሱስን ለ30 ብር አሳልፎ ሰጠ ኢየሱስም ስለ ሰው ልጆች ሀጢያት ነፍሱን የሚሰጥበት ሰዓት እንደረሰ አውቆ ይፀልይ ነበር፡፡ አባት ሆይ ፈቃድህ ቢሆን ይህች ፅዋ ከኔ ትለፍ ነገር ግን የኔ ሳይሆን ያንተ ፈቃድ ይፈፀም ከሰማይም መጥቶ የሚያበረታው መልአክ ታየው አፅንቶም በጣር ሲፀልይ ወዙም በምድር ላይ እንደሚወርድ እንደ ደም ነጠብጣብ ነበር ስለ ምን ትተኛላችሁ፡፡ ንቁ ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ፀልዩ ፡፡ ይሁዳ የሰውን ልጅ በመሳም አሳልፈህ ትሰጣለህን? ጌታ ሆይ በሰይፍ እንምታቸውን? ኑና ያዙት ይበቃል! ታአምር ነው ወንበዴን እንደምትይዙ ሰይፍና ገመድ ይዛችሁ መጣችሁን? በመቅደስ እለት እለት ከእናንተ ጋር ስሆን እጃችሁን አልዘረጋችሁም ነገር ግን ጨለማ በነገሰበት የስራ ጊዜያችሁ ነው። እሰረው በደንብ ጠብቀው ኢየሱስንም የያዙት ሰዎች ወደ ሸንጎ አቅርበው ይዘብቱበትና ይመቱት ነበር ይኸው ግርማዊነትዎ የንጉስ ካባ ምን እንደሚሆን ስለ ወደፊቱ ንገረን ግርማዊነትዎ ያድኑናል ወይ? ያድኑናል ወይ? ይህ ሰው ከኢየሱስ ጋር ነበር ሴትዮ የምትይውን ሰው እኔ አላውቀውም አንድ ላይ አይቻቸዋለሁ ታዛዥ አገልጋዮችህ የተከበሩኛል ምን ይመስልሃል አንተም ከነሱ አንዱ ነህ በፍፅም አይደለሁም እርሱ የገሊላ ሰው ነው በእውነት ይደግሱ ጋር ነበረ ሂድ ከዚህ ስለምን እንደምትናገር አላውቅም ኢየሱስም ዘወር ብሎ በቀጥታ ጴጥሮስን አየው ጴጥሮስም ጌታ፣ ዛሬ ለሊት ዶሮ ሳይጮህ ሶስቴ ትክደኛለህ ያለው ትዝ አለው፡፡ እግዚአብሔር ሆይ! እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ እንደ ምህረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ፥ ከበደሌ ፈፅሞ እጠበኝ እውነትንም ከሰው ልብ ትሻለህ እግዚአብሔር ሆይ! ንፁሕ ልብን ፍጠርልኝ። የማዳንህን ደስታ እንደገና ስጠኝ! በእሽታ መንፈስ ደግፈኝ። ማነው የመታህ እወቅ ትንቢት ተናገር ቀጥሎ ማን ይመታሀል አቁም አቁም ብዬሀለሁ ወደ ሸንጎ አምጥጡት ሂድ የሐይማኖት መሪዎችና ሽማግሌዎች ኢየሱስን ለጥያቄ አቀረቡት ንገረን አንተ መሲሁ ነህን? ብነግራችሁ አታምኑኝም። ጥያቄም ብጠይቃችሁ አትመልሱልኝም ነገር ግን ካሁን ጀምሮ የሰው ልጅ በእግዚአብሄር ሀይል ቀኝ ይቀመጣል ለመሆኑ አንተ የእግዚአብሄር ልጅ ነህን? አንተ እንዳልከው ነው ያንን ለማለት ማን ስልጣን ሰጠው? እግዚአብሔርን እየተሳደበ እኮ ነው ጥፋተኛ ነው ያለውን እኛ በጆሮአችን ሰምተናል፡፡ ወደ ጲላጦስ እንወስደዋለን አስወጣው አዎ አስወጣው ቀጥል ከዚያ ወደ ጴንጤናዊው ጲላጦስ ወሰዱት ይህ ሰው ከሮማውያን ሁሉ ለብዙ ሺ ሰዎች መስቀል ምክንያት የሆነ ሰው ነበር በዚህ ማለዳ ምን ፈልጋችሁ ነው እዚህ የመጣችሁት? ይህ ሰው ህዝቡን ሲያሳምፅ ያዝነው በቤተመቅደስ ገበያ ታላቅ ረብሻን ፈጥሮአል ታዲያ ቅጣቱ ምን መሆን አለበት? ፍረድበት በዚህ ሰው ላይ የምፈርድበት ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም፤ ምንም ይህ ህዝባችንን ሲያጣምም ለቄሳርም ግብር እንዳይሰጥ ሲከልክል እኔ ክርስቶስ ንጉስ ነኝ ሲል አግኝተነዋል ንጉስ! ንጉስ! አንተ የአይሁድ ንጉስ ነህን? አንተ አልህ ከገሊላ ነው ማስተማር የጀመረው አሁን ደግሞ ወደዚህ መጣ በገሊላ? ይህ ሰው ገሊላዊ ነውን? ስለዚህ ነገሩን ሄሮድስ ይመልከተው እሱ አሁን በየሩሳሌም ነው ወደ ሄሮድስ ውሰዱት አንተ ራስህን ማነኝ ትላለህ ደቀመዛሙርትህስ ማን ይሉሀል ብዙ ታምራትን እንደሰራህ ይወራል እስኪ ለአኔም አድርግልኝ፡፡ ጌታ ሆይ ይህ ሰው ህዝቡን ሁሉ ያሳምፃል ራሱንም ንጉስ ነኝ ብሎ ይጠራል። ይህ ሰውዬ? ንጉስ? ግርማዊነትዎ በደንብ ግረፉት። ወደ ጲላጦስ መልሱት። የራሱ ክፍለ ሃገር ነውና ይህ ሰው ለሞት የሚያበቃው ምንም ነገር አልፈፀመም እኔ ላስገርፈውና ልለቀው ወስኛለሁ። በዚህ የቂጣ በዓል ላይ አንድ ሰው እንድትለቅልን ቃል ገብተህልን ነበር ለኛ በርባንን ፈተህልን አዎ በርባንን! ይህንን ሰው ግን አስወግደው በርባንን ፍታልን ስቀለው! አዎ ስቀለው! አንተ አንተ ውሰዱና ግረፉት። ስቀለው! ስቀለው! ስቀለው! ጲላⶏስ ምን ትጠብቃለህ? ኢየሱስ ነው! ለምን ታሰቃዩታላችሁ? እባካችሁ ተዉት እርሱ ክርስቶስ ነው! ምንም ነገር አላደረገም! አንሳው! ህዝቡ ግን ኢየሱስ እንዲሰቀል በታላቅ ድምፅ አጥብቀው ጮኹ። ስለዚህ ጲላጦስ በኢየሱስ ላይ የሞት ፍርድ ወሰነበት፡፡ በርባንንም ፈታ ኢየሱስን ደግሞ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጣቸው። አንተ ስምህ ማን ነው? ስምዖን ነኝ ከቀሬና ና ወደዚህ ገመዱን ቁረጥ ተሸከም ወደዚህ ና ጌታ ሆይ ፣ ስለ አንተ እናነባለን ፣ እናለቅሳለን። እባክህን ጠጣ ፣ ጠጣ ፡፡ ጠጣ ጌታ ሆይ የኢየሬሳሌም ሴቶች ሆይ ስለኔ አታልቅሱ ግን ስለራሳችሁና ስለ ልጆቻችሁ አልቅሱ በእርጥብ እጨት እንዲህ የሚያደርጉ ከሆኑ፥ በደረቀውስ እንዴት ይሆን? እግዚአብሄር ይርዳህ እንፀልይልሃለን። አብረኸው ሂድ መስቀሉን አንሱ ችካሉን ቸክል ገመዱን ፍታው፡፡ የሚያደርጉትን አያውቁምና አባት ሆይ ይቅር በላቸው እርሱ ሌሎችን አዳነ እስቲ አሁን ራሱን ያድን፡፡ አዎ ራስህን አድን አንተ ክርስቶስ ከሆንከ እስቲ ከመስቀል ውረድ እስቲ ከታምራቶችህ አንዱን አሳየን! ከብዙ መቶ አመታት በፊት ነቢያት እንደተናገሩት ኢየስስ በሁለት ወንበዴዎች መካከል ተሰቀለ፡፡ ይህ ተራ ልብስ ሳይሆን ውድ ልብስ ነው! እዚህ እንሂድ አትቅደደው ልንገርህ እጣ እንጣጣል እድለኛ ነህ እጣውን አግኝተህ አሸንፈሀል፡፡ ይህ የአይሁድ ንጉስ ነው የሚል ፅሁፍ በመስቀሉ ላይ ተለጠፈ፡፡ እስኪ የአይሁድ ንጉስ ከሆንክ ራስህን አድን አንተ መሲሁ አይደለህምን እስኪ ራስህንም እኛንም አድነን፡፡ እግዚአብሄርን አትፈራም እኛስ በጥፋታችን ነው የተፈረደብን እርሱ ግን ምንም ነገር አላጠፋም ጌታ ኢየሱስ ሆይ እንደ ንጉስ በመጣህ ጊዜ አስበኝ እውነት እልሀለሁ ዛሬ ከኔ ጋር በገነት ትሆናለህ፡፡ ስድስት ሰዓትም ያህል ነበረ ፡፡ጨለማም እስከ ዘጠኝ ሰዓት በምድር ሁሉ ላይ ሆነ፡፡ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ ወደታች ከመካከሉ ተቀደደ አባት ሆይ ነፍሴን በእጆችህ አደራ እሰጣለሁ የወታደሮቹም አለቃ የሆነውን ነገር ባየ ጊዜ እንዲህ ሲል እግዚአብሄርን አከበረ ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን። በርግጥ ይህ ሰው ፃድቅ ነበረ የተከበረ የሸንጎ አባል የነበረውና በምክራቸውም ያልተባበረው የአርማቲያው ዮሴፍ የኢየሱስን አካል ለመውሰድ ከላ ጲላጦስ ፍቃድ አገኘ ወስዶም የሰንበት ቀን ከመግባቱ በፊት ከድንጋይ በተወቀ አዲስ መቃብር ውስጥ አኖረው። ይቅርታ አድርጉልን የጌታችንን እሬሳ ፈልገን ነው የመጣነው፡፡ እረዳችሁ ነበር ነገር ግን ሰንበት ሊገባ ስለሆነ ፈጥነን ከዚህ እንሂድ እሁድ ዕለት ማልደውም የጌታን አካል ሽቶ ሊቀቡት መጡ። ድንጋዩም ከመቃብሩ ላይ ተንከባሎ አገኙት። ወደ ውስጥም ሲመለከቱ የጌታ የኢየሱስን አካል አላገኙትም። ህያውን ከሙታን መካከል ለምን ትፈልጋላችሁ? በዚህ የለም ተነስቷል። በገሊላ ሳለ የሰው ልጅ አልፎ በኃጢያተኞች ዘንድ ይሰጣል፥ ይሰቀላልም በሶስተኛውም ቀን ከሞት ይነሳል ብሎ የነገራችሁን አስታውሱ። ይኸውላችሁ! ድንጋዩም ተንከባሎ አገኘነው። ወደ ውስጥ ስንገባ የጌታን አካል አጣነው የለም። የጌታችን አካል ተውስዷል? እናም ሁለት መልዓክት አየን፥ እንደ ፀሐይ የሚያንፀባርቁ በታላቅ ድምፅም ህያውን ከሙታን መካከል ለምን ትፈልጋላችሁ? አሉ ይገርማል። እውነቴን ነው! እመኑን እንጂ! እመኑን እኛ አይተናል እናንተም ሂዱና እዩ መቃብሩ ባዶ ነው። ጴጥሮስ ልታምነን ይገባል፡፡ ጌታችን ተነስቶአል። ኢየሱስ ለሁለቱ ደቀመዛሙርት ታየ እነርሱም በመደነቅ ለሌሎች ለመንገር ተመሰሱ፡፡ ጌታ እንደተናገረው ተነስቶአል ለስምዖን ተገልጦአል በመንገድ ሳለን አላወቅነውም ነበር ነገር ግን እንጀራን ሲቆርስ ልናውቀው ቻልን በኤማኦስ እንዴት ወደዛ ሊሄድ ቻለ ሰላም ለእናንተ ይሁን ስለምን ትፈራላችሁ? ለምንስ ጥርጣሬ ወደ ህሊናችሁ መጣ? ተመለልከቱ እጆቼንና እግሮቼን እኔው ራሴ እንደሆንኩም እዩ ዳስሱኝምና ታውቁኛላችሁ፡፡ እዩ መንፈስ ስጋና አጥንት ፈፅሞ የለውም፡፡ ከእናንተ ጋር በነበርኩ ጊዜ ስለ እኔ የነገርኳችሁ ይህ ነው ይኸው በሙሴ ህግ በነቢያት ትንቢትና በመዝሙርም የተፃፈ ሁሉ ተፈፀመ፡፡ የተፃፈው ክርስቶስ መከራ ይቀበላል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሳል በስሙም ንስሀና የኃጢያት ሥርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአህዛብ ሁሉ ይሰበካል፡፡ እናንተም ለዚህ ምስክሮች ናችሁ፡፡ እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፡፡ እናንተም ሀይል እስክትለብሱ በኢየሩሳሌም ቆዩ፡፡ እግዚአብሄር ይባርካችሁ ይጠብቃችሁም፡፡ ስልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ለኔ ተሰጠኝ፡፡ እንግዲህ ሂዱና አህዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርቴ አድርጉአቸው፡፡ እነሆም እኔ እስከ አለም ፍፃሜ ድረስ ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ፡፡ ከብዙ ዘመናት በፊት ነቢያት በቅዱሳት መጻህፍት እግዚአብሔር ኃጢአተኞን እንዲድንና ከእርሱ ጋር እንዲያስታርቃቸው መሲሁን እንደሚልክ ጽፈው ነበር፡፡ የኢየሱስ ሕይወት በእርግጥት አዳኙ እርሱ መሆኑን ያሳያል ኢሳያስ የተባለው ነቢይ፣ "ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች" ሲል ጻፈ፡፡ ይህም ተፈፀመ፡፡ ማርያምም ገና ድንግል ሆና ሳለ እግዚአብሔር በኃይሉ እንድትጸንስና ኢየሱስንም እንድትወልድ አደረገ፡፡ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ተጻፈ፤ በተአምር መወለዱ፤ እግዚአብሔር "ልጄ" ብሎ የሚጠራው መሲሑ መሆኑን፤ የሚያሳይ የእግዚአብሔር ምልክት ነው። ሰዎች ኢየሱስን ሲመለከቱ የእግዚአብሔርን ማንነትና ኃይል ያያሉ፡፡ ሰዎችን ይፈውሳል ኃጢአታቸውንም ይቅር ይላል፣ በእርሱ ዘላለማዊ መንግስትም ስፍራ እንደሚያዘጋጅላቸው ተስፋን ይሰጣል፡፡ ኢየሱስ ለሰው ልጆች ሁሉ ተሰቃየ ሕይወቱንም መስዋዕት አደረገ፡፡ የእርሱም ኃይል ከሞት ኃይል የሚበልጥ መሆኑን ለማሳየት ሕያው ሆነ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ "ሕይወቴን ላኖራት ሥልጣን አለኝ ላነሳትም ሥልጣን አለኝ" ሲል ተናገረ የኢየሱስ ሕይወት የነቢያት ትንቢት ፍጻሜ ሲሆን፤ የእግዚአብሔር ቅዱስ ቃልም ነቢያቱ እንደተናገሩለት እንከን የለሽና ዘላለማዊ መሆኑን አረጋግጦአል፡፡ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው። በኢየሱስም አማካኝነት እግዚአብሔር ራሱን ለዓለም ገልጧል። እግዚአብሔር በመጀመሪያ ወንድንና ሴትን ሲፈጥራቸው የነበረውን የተትረፈረፈ ሕይወት መልሶ ሊሰጠን ኢየሱስ መጣ፡፡ እነርሱ ግን እግዚአብሔርን አልታመኑም ትዕዛዛቱንም አልጠበቁም፡፡ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ተጻፈው፤ "ሰዎች ሁሉ ኃጢአትን ሰርተዋል" "የኃጢአትም ደመወዝ ውጤት ሞት ነው"፡፡ ኃጢአት ያደረጉ ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር በመልካም ግንኙነት መኖር አይችሉም፡፡ እግዚአብሔር ግን በአብርሃም ልጅ ምትክ እንዲሞት አውራ በግ እንደሰጠ ሁሉ፤ በአዳም ዘር ምትክ እንዲሞት ኢየሱስን ላከው፡፡ ይህንንም ያደረገው በኢየሱስ የሚያምኑ ሁሉ ወደ እግዚአብሔር መገኘት መግባት ይችሉ ዘንድ ነው፡፡ ስለዚህም ኢየሱስን የሚከተሉ ሰዎች ከሲዖል ፍርድ አምልጠው ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላለም ይኖራሉ፡፡ ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ በኋላ ለተከታዮቹ "ንስሐ ለሚገቡና ወደ እርሱ ለሚመለሱ እግዚአብሔር የኃጢአትን ስርየት እንደሚሰጥ ሰዎች በስሜ ለአህዛብ ሁሉ ይሰብካሉ" ሲል ተናገረ። በተጨማሪም ኢየሱስ ከተከታዮቹ ጋር እንዲሆን፤ ወደ እውነት ሁሉ እንዲመራቸውና የእግዚአብሔርንም መንገድ እንዲከተሉ ኃይልን እንዲሰጣቸው ቅዱሱን የእግዚእብሔርን መንፈስ እንደሚልክላቸው ተናገረ፡፡ አንዲት ኃጢአተኛ ሴት ንስሓ ገብታ ኢየሱስን ጌታዋ አድርጋ ስትከተል ኢየሱስ "ኃጢአትሽ ተሰርዮልሻል፤ በእኔም ያለሽ እምነት አድኖሻል" አላት። ማንኛውም ሰው በኢየሱስ ካመነ በእግዚአብሔር ፀጋ ይድናል። ኢየሱስ ኃጢአትን ይቅር ለማለት ሥልጣን አለው። የኢየሱስ ተከታይ ለመሆን የወሰኑ ሰዎች እምነታቸውን ለመግለፅ የሚከተሉትን ቃላት በመጠቀም ከኢየሱስ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ሊጀምሩ ይችላሉ፡፡ እግዚእብሔር አባት ሆይ፣ አንተ ጻድቅነህ፡፡ ስለምትወደኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ ትዕዛዛትህን ስላልፈፀምኩና አንተን ስለበደልኩህ እጅግ አዝኛለሁ፡፡ ኢየሱስን በእኔ ምትክ በመስቀል ላይ እንዲሞትና ከሞትም እንዲነሳ ስለላክህልኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ እኔም ስለ ሠራሁት ኃጢአት ስለተሰቃየልኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ የአንተን መንገድ መከተል እፈልጋለሁ ኢየሱስንም አዳኜና ጌታዬ አድርጌ እቀበላለሁ፡፡ ኃጢአቴንም ይቅር ስላልከኝና ወደ አንተም እንድመጣና በመንግስትህም ከአንተ ጋር ለዘላለም እንድኖር በሩን ስለከፈትክልኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ ቅዱሱን መንፈስህን እንድትሰጠኝ ከእኔም ጋር በመኖር መንገድህን እንዲያሳየኝ በሙሉ ልቤ እንድወድህና አንተንም ደስ የሚያሰኝ ሕይወት እንድኖር ኃይልን እንዲሰጠኝ እለምንሃለሁ፡፡ በዚህ ምድር የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በሁሉም ስፍራ ያመሰግኑህ አሜን፡፡ ኢየሱስ ስለተከታዮቹ ሲናገር "በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ፤ እኔም አውቃቸዋለሁ እነርሱም ይከተሉኛል" አለ፡፡ የኢየሱስ ተከታዮች እርስ በርስ ይገናኛሉ፤ በየዕለቱም ከእርሱ ጋር ይነጋገራሉ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት የተጠቀሱትን የእርሱን ቃሎች ያጠናሉ፣ የእርሱንም መንገድ መከተል ይሻሉ፣ ለሌሎችም ስለ እርሱ ይናገራሉ፡፡ በደመናትም ወደ ሰማይ ወደከበረው ዙፋኑ ከማድረጉ በፊት እየሱስ ለተከታዮቹ እግዚአብሔር በሰማይና በምድር ያለውን ሥልጣን ሁሉ ሰጥቶኛል … እስከ ዓለም ፍፃሜም ድረስ ዘወትር ከእናንተ ጋር እንደሆንሁ እርግጠኛ ሁኑ ብሎ የተናገረውን ዘወትር ያስታውሳሉ፡፡
JesusFilm