Easter·22 ከ 22

Invitation to Know Jesus Personally

A narrator gives an invitation to know God personally. The invitation is open to everyone. It means turning to God and trusting Jesus with our lives and to forgive our sins. We can speak to Him in prayer when we're ready to become followers of Jesus.

የእርስዎን ይጠይቁ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

አጋራ
ነፃ ምንጮች

መጽሐፍ ቅዱስን ይበልጥ በጥልቀት ማስተዋል ይፈልጋሉ?

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችንን ይቀላቀሉ

ጽሑፍ ቅጂ

Amharic (ኣማርኛ)
ከብዙ ዘመናት በፊት ነቢያት በቅዱሳት መጻህፍት እግዚአብሔር ኃጢአተኞን እንዲድንና ከእርሱ ጋር እንዲያስታርቃቸው መሲሁን እንደሚልክ ጽፈው ነበር፡፡ የኢየሱስ ሕይወት በእርግጥት አዳኙ እርሱ መሆኑን ያሳያል ኢሳያስ የተባለው ነቢይ፣ "ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች" ሲል ጻፈ፡፡ ይህም ተፈፀመ፡፡ ማርያምም ገና ድንግል ሆና ሳለ እግዚአብሔር በኃይሉ እንድትጸንስና ኢየሱስንም እንድትወልድ አደረገ፡፡ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ተጻፈ፤ በተአምር መወለዱ፤ እግዚአብሔር "ልጄ" ብሎ የሚጠራው መሲሑ መሆኑን፤ የሚያሳይ የእግዚአብሔር ምልክት ነው። ሰዎች ኢየሱስን ሲመለከቱ የእግዚአብሔርን ማንነትና ኃይል ያያሉ፡፡ ሰዎችን ይፈውሳል ኃጢአታቸውንም ይቅር ይላል፣ በእርሱ ዘላለማዊ መንግስትም ስፍራ እንደሚያዘጋጅላቸው ተስፋን ይሰጣል፡፡ ኢየሱስ ለሰው ልጆች ሁሉ ተሰቃየ ሕይወቱንም መስዋዕት አደረገ፡፡ የእርሱም ኃይል ከሞት ኃይል የሚበልጥ መሆኑን ለማሳየት ሕያው ሆነ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ "ሕይወቴን ላኖራት ሥልጣን አለኝ ላነሳትም ሥልጣን አለኝ" ሲል ተናገረ የኢየሱስ ሕይወት የነቢያት ትንቢት ፍጻሜ ሲሆን፤ የእግዚአብሔር ቅዱስ ቃልም ነቢያቱ እንደተናገሩለት እንከን የለሽና ዘላለማዊ መሆኑን አረጋግጦአል፡፡ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው። በኢየሱስም አማካኝነት እግዚአብሔር ራሱን ለዓለም ገልጧል። እግዚአብሔር በመጀመሪያ ወንድንና ሴትን ሲፈጥራቸው የነበረውን የተትረፈረፈ ሕይወት መልሶ ሊሰጠን ኢየሱስ መጣ፡፡ እነርሱ ግን እግዚአብሔርን አልታመኑም ትዕዛዛቱንም አልጠበቁም፡፡ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ተጻፈው፤ "ሰዎች ሁሉ ኃጢአትን ሰርተዋል" "የኃጢአትም ደመወዝ ውጤት ሞት ነው"፡፡ ኃጢአት ያደረጉ ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር በመልካም ግንኙነት መኖር አይችሉም፡፡ እግዚአብሔር ግን በአብርሃም ልጅ ምትክ እንዲሞት አውራ በግ እንደሰጠ ሁሉ፤ በአዳም ዘር ምትክ እንዲሞት ኢየሱስን ላከው፡፡ ይህንንም ያደረገው በኢየሱስ የሚያምኑ ሁሉ ወደ እግዚአብሔር መገኘት መግባት ይችሉ ዘንድ ነው፡፡ ስለዚህም ኢየሱስን የሚከተሉ ሰዎች ከሲዖል ፍርድ አምልጠው ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላለም ይኖራሉ፡፡ ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ በኋላ ለተከታዮቹ "ንስሐ ለሚገቡና ወደ እርሱ ለሚመለሱ እግዚአብሔር የኃጢአትን ስርየት እንደሚሰጥ ሰዎች በስሜ ለአህዛብ ሁሉ ይሰብካሉ" ሲል ተናገረ። በተጨማሪም ኢየሱስ ከተከታዮቹ ጋር እንዲሆን፤ ወደ እውነት ሁሉ እንዲመራቸውና የእግዚአብሔርንም መንገድ እንዲከተሉ ኃይልን እንዲሰጣቸው ቅዱሱን የእግዚእብሔርን መንፈስ እንደሚልክላቸው ተናገረ፡፡ አንዲት ኃጢአተኛ ሴት ንስሓ ገብታ ኢየሱስን ጌታዋ አድርጋ ስትከተል ኢየሱስ "ኃጢአትሽ ተሰርዮልሻል፤ በእኔም ያለሽ እምነት አድኖሻል" አላት። ማንኛውም ሰው በኢየሱስ ካመነ በእግዚአብሔር ፀጋ ይድናል። ኢየሱስ ኃጢአትን ይቅር ለማለት ሥልጣን አለው። የኢየሱስ ተከታይ ለመሆን የወሰኑ ሰዎች እምነታቸውን ለመግለፅ የሚከተሉትን ቃላት በመጠቀም ከኢየሱስ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ሊጀምሩ ይችላሉ፡፡ እግዚእብሔር አባት ሆይ፣ አንተ ጻድቅነህ፡፡ ስለምትወደኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ ትዕዛዛትህን ስላልፈፀምኩና አንተን ስለበደልኩህ እጅግ አዝኛለሁ፡፡ ኢየሱስን በእኔ ምትክ በመስቀል ላይ እንዲሞትና ከሞትም እንዲነሳ ስለላክህልኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ እኔም ስለ ሠራሁት ኃጢአት ስለተሰቃየልኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ የአንተን መንገድ መከተል እፈልጋለሁ ኢየሱስንም አዳኜና ጌታዬ አድርጌ እቀበላለሁ፡፡ ኃጢአቴንም ይቅር ስላልከኝና ወደ አንተም እንድመጣና በመንግስትህም ከአንተ ጋር ለዘላለም እንድኖር በሩን ስለከፈትክልኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ ቅዱሱን መንፈስህን እንድትሰጠኝ ከእኔም ጋር በመኖር መንገድህን እንዲያሳየኝ በሙሉ ልቤ እንድወድህና አንተንም ደስ የሚያሰኝ ሕይወት እንድኖር ኃይልን እንዲሰጠኝ እለምንሃለሁ፡፡ በዚህ ምድር የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በሁሉም ስፍራ ያመሰግኑህ አሜን፡፡ ኢየሱስ ስለተከታዮቹ ሲናገር "በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ፤ እኔም አውቃቸዋለሁ እነርሱም ይከተሉኛል" አለ፡፡ የኢየሱስ ተከታዮች እርስ በርስ ይገናኛሉ፤ በየዕለቱም ከእርሱ ጋር ይነጋገራሉ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት የተጠቀሱትን የእርሱን ቃሎች ያጠናሉ፣ የእርሱንም መንገድ መከተል ይሻሉ፣ ለሌሎችም ስለ እርሱ ይናገራሉ፡፡ በደመናትም ወደ ሰማይ ወደከበረው ዙፋኑ ከማድረጉ በፊት እየሱስ ለተከታዮቹ እግዚአብሔር በሰማይና በምድር ያለውን ሥልጣን ሁሉ ሰጥቶኛል … እስከ ዓለም ፍፃሜም ድረስ ዘወትር ከእናንተ ጋር እንደሆንሁ እርግጠኛ ሁኑ ብሎ የተናገረውን ዘወትር ያስታውሳሉ፡፡
JesusFilm