Easter·4 ከ 29

Why Did Jesus Have to Die?

God created humans to be spiritually and relationally connected with Him, but how can we keep God's commands? How can we live without shame? We can't restore ourselves to honor. It would seem we're doomed, except God doesn't want His creation to die. He is merciful and loving, and wants us to be restored, living with Him in full life.

የእርስዎን ይጠይቁ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

አጋራ
Isaiah 53:5

But He was pierced for our transgressions, He was crushed for our iniquities; the punishment that brought us peace was upon Him, and by His stripes we are healed.

Berean Standard Bible

Public Domain

ተጨማሪ አንብብ...
ነፃ ምንጮች

መጽሐፍ ቅዱስን ይበልጥ በጥልቀት ማስተዋል ይፈልጋሉ?

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችንን ይቀላቀሉ

ጽሑፍ ቅጂ

Amharic (ኣማርኛ)
ሀጥያት፤ በሰዎች መካከል መከፋፈልን የሚያመጣ እና እኛን ከእግዚአብሔር የሚለየን ግድግዳ። ሰዎች ለሚያደርጎቸው ድርጊቶች ተጠያቂዎች ከሆኑ እና ሀጥያትን ቢያደርጉ በስራቸው ተጠያቂ መሆን ሲገባቸው ለምን እግዚአብሔር ያድናቸዋል? እግዚአብሔር ፍቅር ነው፤ ህይወትን ሰጪ ነው። እርሱ ሰዎችን የፈጠረው በመንፈስ እና በግኑኝነት ከእርሱ ጋር መጣበቅ እንዲችሉ ነው። ነገር ግን የሰው ዘር ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጪ ለመሆን እና ሀጥያትን ለማድረግ መረጠ የህይወት ምንጭ ከሆኑው ከእግዚአብሔር ለየን ሀጥያት እንደ ቫይረስ ከትውልድ ወደ ትውልድ ተላለፈ ከሰብአዊነት ጋር የተስፋፋ ሰዎችን ከእግዚአብሔር እና ከእርስበእርሱ የለየ ነው እግዚአብሔር በነብያቶቹ እየተናገረ የእርሱን ህግ እንዲከተሉ አዲስ ትዕዛዛት እና እድሎች ሰጠ ነገር ግን ሰዎች ይህንን ማድረግ አልቻሉም። የሀጥያት ዋጋ፤ እኛን ከእግዚአብሔር ጋር መለየት እና ሞት ነው እግዚአብሔር ፍፁም ጻዲቅ በመሆኑ የሰውን ሁሉ ሀጥያት ችላ ማለት ወይም መማር አይችልም። እግዚአብሔር ቅዱስ እና ጻዲቅ ነው የእርሱ ያለ ምንም ማመቻመች ሀጥያትን ላይ መፍረድ እና ሀጥያትን መቅጣት አለበት ስለዚህ የእግዚአብሔር ምህረት እንዲገባን እና ከፍርድ እንድናመልጥ ማድረግ የእኛ ድርሻ አይመስላችሁም? ችግሩ ሰው የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ መጠበቅ እና ከሀጥያት ውጪ መኖር አይችልም እና እኛ እራሳችንን ማዳን አንችልም የምንጠፋ ይመስለናል እግዚአብሔር ግን የእርሱ ፍጥረታት እንዲሞት አይፈልግም። እርሱ በምህረት የተሞላ እና አፍቃሪ ሲሆን ታድሰን ከእርሱ ጋር ሙሉ የሆነ ህይወት እንድንኖር ይፈልጋል። በአብርሃም ጀምሮ ባለፉት አመታት በሌሎች ነብያትም ቀጥሎል እግዚአብሔር የሰውን ዘር የሀጥያት ቅጣት ማን ሊከፍል የሚችል አዳኝ የመላክ እቅዱን ቀስ በቀስ ገለጠ አዳኙ ኢየሱስ ነው። እርሱ በሰማይ ካለው የክብር ስፍራ ወደ ምድር ወረደ፤ የሰውን ስጋ ለበሰ እና እኛ መኖር የማንችለውን ሀጥያት የሌለበትን ህይወት ኖረ ከዛም ኢየሱስ በገዛ ፈቃዱ ሀጥያታችንን ወሰደ፤ የእኛን የሞት ቅጣት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ከእኛ ወሰደ ነገር ግን በሞት ሊያዝ አልቻለም። ኢየሱስ ሞትን እና ሀጥያትን አሽንፎ ከመቃብር ተነሳ እኛ ከእግዚአብሔር ጋር የታደሰ ግኑኝነት እንዲኖረን አስቻለን እግዚአብሔር ይወደናል፤ የሰው ልጆች እራሳቸውን ማደስ ብቃት ስለሌላቸው ኢየሱስ እንድንድን እና ከእርሱ ጋር መኖር እንድንችል ከሀጥያት እና ከሞት አዳነን አሁን እኛ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን የታደሰ ግኑኝነት እና ነፃነት ማጣጣም እንድንችል ኢየሱስ ስለ እኛ የከፈለውን መሰዋዕትነት መቀበል አለብን
JesusFilm