1 ከ 61JESUS · 61 ምዕራፎች

The Beginning

The story of Jesus fits within the larger story of the Judeo Christian tradition. The purpose of everything since creation has been to point to the life of Jesus. All of creation speaks of the majesty of God. As God created man and woman he intended them to live in peace with him forever. But because of their disobedience mankind was separated from God. But God still loved mankind so throughout the Scriptures God reveals his plan to save the world.

የእርስዎን ይጠይቁ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

አጋራ
Genesis 1:26-27

Then God said, “Let Us make man in Our image, after Our likeness, to rule over the fish of the sea and the birds of the air, over the livestock, and over all the earth itself and every creature that crawls upon it.” So God created man in His own image; in the image of God He created him; male and female He created them.

Berean Standard Bible

Public Domain

ተጨማሪ አንብብ...
Genesis 3:7

And the eyes of both of them were opened, and they knew that they were naked; so they sewed together fig leaves and made coverings for themselves.

Berean Standard Bible

Public Domain

ተጨማሪ አንብብ...
Genesis 3:22-24

Then the Lord God said, “Behold, the man has become like one of Us, knowing good and evil. And now, lest he reach out his hand and take also from the tree of life, and eat, and live forever...” Therefore the Lord God banished him from the Garden of Eden to work the ground from which he had been taken. So He drove out the man and stationed cherubim on the east side of the Garden of Eden, along with a whirling sword of flame to guard the way to the tree of life.

Berean Standard Bible

Public Domain

ተጨማሪ አንብብ...
Genesis 22:1-18

Some time later God tested Abraham and said to him, “Abraham!” “Here I am,” he answered. “Take your son,” God said, “your only son Isaac, whom you love, and go to the land of Moriah. Offer him there as a burnt offering on one of the mountains, which I will show you.” So Abraham got up early the next morning, saddled his donkey, and took along two of his servants and his son Isaac. He split the wood for a burnt offering and set out for the place God had designated. On the third day Abraham looked up and saw the place in the distance. “Stay here with the donkey,” Abraham told his servants. “The boy and I will go over there to worship, and then we will return to you.” Abraham took the wood for the burnt offering and placed it on his son Isaac. He himself carried the fire and the sacrificial knife, and the two of them walked on together. Then Isaac said to his father Abraham, “My father!” “Here I am, my son,” he replied. “The fire and the wood are here,” said Isaac, “but where is the lamb for the burnt offering?” Abraham answered, “God Himself will provide the lamb for the burnt offering, my son.” And the two walked on together. When they arrived at the place God had designated, Abraham built the altar there and arranged the wood. He bound his son Isaac and placed him on the altar, atop the wood. Then Abraham reached out his hand and took the knife to slaughter his son. Just then the angel of the Lord called out to him from heaven, “Abraham, Abraham!” “Here I am,” he replied. “Do not lay a hand on the boy or do anything to him,” said the angel, “for now I know that you fear God, since you have not withheld your only son from me.” Then Abraham looked up and saw behind him a ram in a thicket, caught by its horns. So he went and took the ram and offered it as a burnt offering in place of his son. And Abraham called that place The Lord Will Provide. So to this day it is said, “On the mountain of the Lord it will be provided.” And the angel of the Lord called to Abraham from heaven a second time, saying, “By Myself I have sworn, declares the Lord, that because you have done this and have not withheld your only son, I will surely bless you, and I will multiply your descendants like the stars in the sky and the sand on the seashore. Your descendants will possess the gates of their enemies. And through your offspring all nations of the earth will be blessed, because you have obeyed My voice.”

Berean Standard Bible

Public Domain

ተጨማሪ አንብብ...
Psalm 19:1-2

For the choirmaster. A Psalm of David. The heavens declare the glory of God; the skies proclaim the work of His hands. Day after day they pour forth speech; night after night they reveal knowledge.

Berean Standard Bible

Public Domain

ተጨማሪ አንብብ...
ነፃ ምንጮች

መጽሐፍ ቅዱስን ይበልጥ በጥልቀት ማስተዋል ይፈልጋሉ?

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችንን ይቀላቀሉ

ጽሑፍ ቅጂ

Amharic (ኣማርኛ)
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ዓለምን ፈጠረ፤ እርሱም ሰማያትንና ምድርን በውስጣቸው ያለውን ሁሉ ፈጠረ፡፡ እግዚአብሔር የሠራውን ሥራ ሁሉ ስንመለከት እጅግ እንደነቃለን፡፡ እግዚአብሔር የሠራው ሁሉ መልካም ነበር፡፡ ሁሉ የእርሱን ታላቅነት፣ መልካምነትና ኃይል ይገልጣሉ፡፡ እግዚአብሔር የተለያዩ ዝርያ ያላቸውን የዕጽዋትንና እንስሰሳት ሁሉ ፈጠረ ከዚያም የመጀመሪያውን ሰው ከምድር አፈር አበጀው፡፡ በአፍንጫውም የሕይወትን እስትንፋስ እፍ አለበት ሕይወትንም ሰጠው ይህም የመጀመሪያው ሰው አዳም ይባላል ከዚያ እግዚአብሔር ሴትን የአዳም ሚስትና ረዳት እንድትሆን ፈጠራት፡፡ ሔዋን ተብላም ተጠራች፡፡ እግዚአብሔርም ወንድና ሴት አድርጎ በአምሳሉ ፈጠራቸው ስለዚህም ከእርሱ ጋር የቅርብ ግንኙነት ነበራቸው፡፡ ውብ በሆነችው ገነት ውስጥ ከእርሱ ጋር በደስታ ይኖሩ ነበር፡፡ በዚያም መከራና ሞት አልነበረም፡፡ እግዚአብሔር አዳምን "ከአንዷ በስተቀር ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፡፡ ከእርሷ በበላህ ቀን ግን ትሞታለህ" አለው፡፡ ነገር ግን አንድ ቀን ሰይጣን የአጋንንቶች አለቃ ሔዋንን ፈተናት፡፡ እርሷም ከፍሬው ጥቂት ወስዳ በላች ባሏም ደግሞ በላ፡፡ በዚያች ቅጽበት ከእግዚአብሔር ጋር የነበራቸው ግንኙነት ተቋረጠ እግዚአብሔር ቅዱስ ነው፣ ኃጢአተኞች ከእርሱ ጋር መኖር አይችሉም፡፡ እግዚአብሔርም አዳምንና ሔዋንን ገነት አባረራቸው፡፡ እግዚአብሔርን ባለመታዘዛቸው ይህ ሁሉ ኃፍረት መጣባቸው፡፡ በውጤቱም አዳምና ሔዋን፣ ዘራቸውም በጠቅላላ በህመምና በሞት ይሰቃይ ጀመር፡፡ እግዚአብሔር ግን ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር አልቀነሰም፡፡ ስለዚህም ተመልሰው ከእርሱ ጋር መኖር የሚችሉበትን መንገድ አዘጋጀ፡፡ እግዚአብሔር የሰውን ዘር ከኃጢአት ለማዳን ያዘጋጀውን እቅድ በቅዱሳት መጻፍት በኩል አስታውቋል። እግዚአብሔርም ከዕቅዱ መካከል አንዱን ክፍል ለነቢዩ አብርሃም አሳወቀ። አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ አከበረውም፡፡ እግዚአብሔርም እንደሚባርከውና የምድርንም ህዝቦች ሁሉ በእርሱ በኩል እንደሚባርክ ቃል ገባለት፡፡ በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ በሰማይ እንዳሉ ከዋክብት ... ዘሩንም እንደሚያበዛለት ቃል ገባለት። አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ፡፡ ከእምነቱም የተነሳ እግዚአብሔር ጻድቅ ነህ ብሎ አወጀለት፣ ሰዎችም "የእግዚአብሔር ወዳጅ" ብለው ጠሩት አንድ ቀን እግዚአብሔር በእርሱ መታመኑንና ትዕዛዛቱንም እንደሚጠብቅ ለማወቅ አብርሃምን ፈተነው፡፡ ልጁንም ወስዶ እንዲሰዋለት አዘዘው፡፡ አብርሃምም በዚሁ አንድ ልጁ በኩል ዘሩ እንደሚበዛ እግዚአብሔር ቃል እንደገባለት እያወቀ እግዚአብሔርን በማመን ታዘዘ፡፡ ስለዚህም ልጁን ለእግዚአብሔር መስዋዕት አድርጎ ለመግደል ተዘጋጀ፡፡ እግዚአብሔር ግን "አብርሃም! በልጁ ላይ አንዳች አታድርግበት፡፡]Nእኔን እንደምትፈራና ልትታዘዘኝም ዝግጁ እንደሆንክ አወቅሁ" አለው አብርሃምም አንድ አውራ በግ አየ፡፡ ቀንዶቹም በቁጥቋጦ ተጠላልፈው ነበር፡፡ አብርሃምም እግዚአብሔር ያዘጋጀውን አውራ በግ ወስዶ በልጁ ምትክ ለእግዚአብሔር መስዋዕት አደረገው፡፡ እግዚአብሔር በጉን በአብርሃም ልጅ ምትክ መስዋዕት ሆኖ እንዲሞት በማቅረብ፤ ለሰዎች ያለውን ታላቅ ፍቅር አሳየ፡፡ የእርሱም ፍቅር መልካም አባት ለልጆቹ ያለውን አይነት ነው በዚህም እግዚአብሔር በሰው ልጆች ምትክ የፍፃሜ መስዋዕት ለማቅረብ ያዘጋጀውን ዕቅድ ገለጠ፡፡ ከብዙ ዘመናት በፊት እግዚአብሔር የአዳምን ዘር ኃጢአትና ኃፍረት እንዲያስወግድ፤ በእነርሱም ምትክ መስዋዕት እንዲሆን አንዳች ኃጢአት የሌለበትን ሰው እንደሚልክ ለነቢያት ገለጠላቸው፡፡ የእርሱም፣ ስዋዕትነት በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር በህብረት ለዘላለም መኖር የሚችሉበትን መንገድ ይከፍታል፡፡ ነቢያትም ይህንን ሰው "መሲሁ" ብለው ይጠሩታል፡፡ እግዚአብሔር ሰዎችን እንዲያድንና በእግዚአብሔር ስም ለዘለዓለም እንዲገዛቸው መሲሁን ይልካል ብለው ተናገሩ፡፡ ከመምጣቱ ከብዙ መቶ አመታት ቀደም ብሎ፣ ነቢያቱ መሲሁ ስለሚያከናውናቸው ተግባራትና በእርሱም ላይ ስለሚደርስበት ነገሮች ተናገሩ፡፡ ከነቢያት አንዱም እግዚአብሔር መሲሁን "አንተ ልጄ ነህ" ብሎ አወጀ ሲል ይናገራል፡፡ "የእግዚአብሔር ልጅ" የሚለው መጠሪያ መሲሁ ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን የቅርብ ግንኙነትና እንደ አዳኝና ንጉስ ያለውን ድርሻ የሚያመለክት ነው፡፡ ኢሳያስ የተባለው ነቢይ ደግሞ "ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች" ሲል ተናረገ፡፡ ይህም ልጅ የእግዚአብሔር ዘላላማዊ ቃል ሲሆን እግዚአብሔርም ሰው ሆኖ እንዲወለድና እግዚአብሔርን ለዓለም እንዲገልጥ ወደ ድንግል የላከው ነው፡፡ በተጨማሪም ነቢያቱ መሲሁ በቤተልሔም እንደሚወለድ ተናግረዋል፡፡ ወደ ኢየሩሳሌም እንደ ንጉሥ እንደሚገባ እና… ከወዳጆቹ በአንዱ እንደሚከዳና በ30 ብር እንደሚሸጥ አስቀድመው ተንብየዋል፡፡ ነቢያቱ መሲሁ ሕይወቱን መስዋዕት እንደሚያደርግ እግዚአብሔር ግን በሦስተኛው ቀን ከሙታን እንደሚያስነሳው ተናግረዋል፡፡ ነቢያቱም መሲሁን "የሰው ልጅ" ብለው ይጠሩታል ደግሞም ደመናትን ሰንጥቆ እግዚአብሔር ወዳለበት እንደሚመለስ እና እግዚአብሔር በህዝቦች ሁሉ ላይ የዘላለም ሥልጣን እንደሚሰጠው ተናግረዋል፡፡ ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት በዚህ ምድር የኖረ ስሙ ኢየሱስ የተባለ አንድ ሰው ነበረ፡፡ ሰዎችም እርሱ የሚያደርጋቸውን ነገሮች ባዩ ጊዜ እርስ በርሳቸው "ይህ ሰው መሲሁ ይሆንን?" "የኢየሱስ ሕይወት ነያብቱ ስለ መሲሁ የተናገሩት ፍፃሜ ይሆንን?" ይባባሉ ነበር፡፡ ይህ ፊልም ኢየሱስ ማን እንደሆነ እርሱ ከተናገራቸውና ካከናወናቸው ጥቂቶቹንና በቅዱሳት መጻህፍት የተጻፉትን ያቀርብላችኋል፡፡ በዚህ ፊልም እንደ ኢየሱስ ሆኖ የተወነው ሰው ነው፡፡ ይህንን ለማድረግ የተገባው ማንም የለም፣ ሆኖም ግን ይህ ፊልም ሰዎች ስለ ኢየሱስ ሕይወት እንዲያውቁና እንዲማሩ ለማድረግ የተዘጋጀ ነው፡፡ በዚሁም እግዚአብሔር ሊሰጥ ተስፋ የገባውን በረከት ይቀበላሉ፡፡
JesusFilm